ጳጉሜ 1 “የኢትዮጵያዊነት ቀን”- በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተከበረ!!

የኮተቤ ሜትሮፖታን ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በስራ ገበታቸው ላይ በመገኘት ጳጉሜ 1ን ከጠዋቱ 2:30 “ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ ” በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ እለቱን አክብረዋል።
በፕሬዝደንት ጽ/ቤ/ት ፊት ለፊት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አመራርና ሰራተኞች፣ የኒቨርሲቲዉ ተማሪዎችና የህብረቱ አመራሮችና የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮች በጋራ በመሆን ከጠዋቱ 2:30 ላይ በመገናኘት የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር እለቱን ያደመቁ ሲሆን፣ በመርኃ-ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የጳጉሜ ቀናቶች ለሃገራዊ አንድነታችንና ክብር የተለየ ትርጉም እንዲኖራቸው ታሳቢ ተደርጎ የተሰየሙ መሆኑን በመግለፅ የእያንዳንዱን ቀን ስያሜ ምንነትና ትርጉም አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በተለይም በከፍተኛ ትምህት ተቋማት ያለን ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ክብር የተረዳ ትዉልድ ከመፍጠር አንፃር ብዙ መስራት እንዳለብን በማሳሰብ ሁላችንም ለኢትዮጵያችን ያለልዩነት በአንድነት ለመቆም ቃል የምንገባበትና በተሰማራንበት የስራ መስክ እንደመከላከያችን ለሃገራችንን ክብር ከመቸውም ጊዜ በላይ ተግተን በመስራት የተግባር ጀግንነትን እንድንጋራ አደራ የተጣለብን መሆኑን አውቀን ቃል የምንገባበት ቀን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *