የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ ከፋይ (self-sponsor) የመጀመሪያ ዲግሪ በ Post Basic ፕሮግራም በቀን በተለያዩ ትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከመስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 05 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የትምህርት መስኮቹ/ፕሮግራሞቹ፣
Surgical Nursing
Family health
Psychiatric Nursing
Operating theatre Nursing
Neonatal Nursing
Anesthesia
Pharmacy
Medical Laboratory Technology
Health Informatics
Pediatric Nursing
Midwifery
Human Nutrition ( generic 4 year)
Nursing
የመግቢያ መስፈርት
- እውቅና ካለው ኮሌጅ በዲፕሎማ ወይም በደረጃ 4 ዲፕሎማቸውን በሚያመለክቱበት የትምህርት ዘርፍ ተዛማጅ በሆነ ትምህርት ያጠናቀቁና የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የመሰናዶ ፈተና የወሰዱ እና የሣይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር በየአመቱ የሚያወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ(ለ Human Nutrition አመልካቾች ብቻ )
- በተጨማሪ በስርአተ ትምህርቱ ላይ ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ
ማሳሰቢያ
ለማመልከት
- የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶኮፒ ማቅረብ
- የማመልከቻ ማይመለስ ብር 100.00 መክፈል
ሲሆን የሚጠበቅባችሁን መስፈርትና ፈተናውን ያለፋችሁ አመልካቾች እስከ ምዝገባ ጊዜ official transcript ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መሪጃ
በስልክ መስመር 251-118704615 ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመደወል ወይም በ ኢሜል አድራሻ፡ mhmc@kmu.edu.et መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬትe