ለሀገራችን አንድ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስፈልጋት በቀረበው ትንታኔ መነሻነት የቀድሞ ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ የ”ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ” እንዲሆን ተወስኗል። ተጠሪነቱም ለኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ለፓርላማው ቀርቦ በአዋጅ ተደንግጓል። ዩኒቨርስቲው ልዩ ባህርይን ተላብሶ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽ ላደረጋችሁ አካላት በሙሉ በራሴ እና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር)
ፕሬዚዳንት