የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሚሰራቸው ጥናቶችና ምርምሮች ውጤታማና ችግር ፈቺ መሆናቸው ተገለፀ፡፡

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ መከላከል ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአዲስ አበባ ከተማንና የአካባቢዋን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ ባለመው የጥናት ኘሮጀክት ዙሪያ ግብዓት ለማሰባሰብ በቶኘ ቴን ሆቴል በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የቀድሞው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የአሁኑ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሚሰራቸው ጥናቶችና ምርምሮች ማህበረሰብ ተኮር፣ ውጤታማና ችግር ፈቺ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡  

ዩኒቨርሲቲው በእስካሁኑ ሂደት ከከተማው አስተዳደር ቢሮዎች ጋር በመተባበር የሰራቸው ጥናቶች በቅርቡ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት በማስመልከት የተሰራውን ጥናት ጨምሮ ሁሉም ጥናቶች ውጤታማ እንደነበሩ የጠቀሱት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና፣ ዩኒቨርሲቲው ጥናቶችንና ምርምሮችን ሲሰራ ለገንዘብ ብሎ ሳይሆን በተግባር የማህበረሰብን ችግር ለመፍታት አልሞ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡በተመሳሳይ መልኩ አሁን እየተሰራ ያለው ስራ የከተማዋን ችግር ሊፈታ የሚችል እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ የገለፁት ኘሬዝዳንቱ ይህ ጥናት የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ወደ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከተቀየረ ወዲህ የመጀመሪያው እንደሚሆንና ለጥናቱም የእስካሁኑ ሂደት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ መከላከል ኮሚሽን ድርሻ ጉልህ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአውደ ጥናቱን ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህብረሰብ ምክትል ኘሬዝዳንት ዶክተር ጠና በቀለ፣ ጥናቱ በሃገራችን ታሪክ የመጀመሪያውና ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራ እንደመሆኑ ለሌሎች ከተሞችም አርአያ ስለሚሆን ለኘሮጀክቱ ስኬታማነት ግብዓት የሚሆን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሙያዊ አስተያየት እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል፡፡ በዚሁ የምክክር መድረክ የጥናቱን ሂደት የሚያመለክቱ መነሻ ትልመ ጥናቶች በዶ/ር በሊና ተርፋሳ፣ በዶክተር ብርሃኑ እንደሻውና በዶክተር ቱሉ ቶላ የቀረበ ሲሆን በጥናት ቡድኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እተየሰራ ያለው ስራ ገና ከጅመሩ ብዙ የታለፈበትና በቀጣይም ሲጠናቀቅ የከተማዋን ብሎም ዙሪያዋ የሚገኙ አካባቢዎችን ችግር ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑንም የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች አስተያየት የተሰጠበት የተሳከ የውይይት መድረክ መሆኑን ለማወቅ ተችላል፡፡  

 

                                                                                                                    የኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት                                                            

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *