ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በየደረጃው ካሉ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር በአዲሱ የተቋማዊ ሽግግር ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት አደረገ፡፡

የቀድሞው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ዓ.ም መወሰኑን ተከትሎ የሽግግር ሂደቱን የሚያሳይ ፍኖተ-ካርታ እንዲያዘጋጅ በዩኒቨርሲቲው የተሰየመው ግብረ-ኃይል ባዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ላይ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል በቀን 12/04/2014 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል።
ሰነዱ ለዩኒቨርስቲ ካውንስሉ ከቀረበ በኃላ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል የትምህርት ዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ፣ አወቃቀርና አደረጃጀት በተመለከተም ለዩኒቨርሲቲው በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ ማዕከል ባደረገ አግባብ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያቀረቧቸውን ሃሳቦችና አስተያየቶች ግብረ-ኃይሉ ግንዛቤ ውስጥ እንዲያስገባና ሰነዱ የበለጠ ዳብሮ መቅረብ እንዲችል አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ሰነዱን ወደ ተግባር በማሸጋገሩ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ የዐብይ ኮሚቴ፣ ቴክኒካል ኮሚቴ እና ሌሎች ኮሚቴዎች የማደራጀት ሥራ መሠራቱን፤ በቀጣይም የትምህርት ዩኒቨርሲቲውን የማደራጀት ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የሚረዱ የሃገሪቱ የትምህርት ልሂቃን አማካሪ የሚሆኑበት ቦርድ እንደሚቋቋምና ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተሳታፊ የሚሆኑባቸው ቀጣይ መድረኮች እንደሚመቻቹ ገልጸዋል።
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *