በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሚኖሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑት ኢንጅነር ደርብ ሸንቁጥ ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ስጦታ አበረከቱ፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያ የሆኑት እጩ ዶክተር ኢንጅነር ደርብ ሸንቁጥ መጻሕፍቱን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ መጻሐፎችን ከስድስት ሲዲዎች ጋር ለማበርከት ያነሳሳቸው ምክንያት የዜግነት ድርሻቸውን ለመወጣት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ስጦታው ለዩኒቨርሲቲው አቅም ግንባታ አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

መጻሕፍቱን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና እጅ የተረከቡት የዩኒቨርሲቲው ቤተ-መጻሕፍትና አካዳሚክ ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ግርማ በበኩላቸው፣ የሀገሪቱ ዜጎች እንደዚህ አስበው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሚገለገሉበትን መጻሕፍት በዚህ መልኩ ማበርከታቸው ለሀገሪቱ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

ሌሎች በውጪው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የኚህን ኢትዮጵያዊ አርአያነት እንዲከተሉና የሚታወሱበትን ለሀገራቸው የሚያበረክቱ እንዲሆኑ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አድርገዋል።

                                                              የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *