ሜጋ አሳታሚና ማከፋፈያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የመጻሕፍት ስጦታ ሰጠ፡፡

ጥር 19/2014 ዓ.ም(ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ)
ሜጋ አሳታሚና ማከፋፈያ ኃ/የተ/የግ/ማህበርን ወክለው የመጻሕፍት ስጦታውን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ለተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ያስረከቡት አቶ ለማ አሸናፊ፣ ኮተቤ ከትናንት እስከ ዛሬ ብዙ ዜጎችን የማፍራት ሀገራዊ ተልዕኮን ላነገበው ለዚህ አንጋፋ ተቋም ማህበሩ ያበረከተው ስጦታ ትንሽ ቢሆንም መጻሕፍቱ ለተማሪዎች ካላቸው ከፍተኛ እገዛ አንፃር ሲታዩ ግን ስጦታው የማይናቅ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ እንደአቶ ለማ ገለፃ ለዩኒቨርሲቲው በስጦታ የተበረከቱት መጻሕፍት አዳዲስና በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ዋጋቸው በገንዘብ ሲተመን 38 ሺህ ብር ይሆናል፡፡
ዶ/ር ብርሃነመስቀል መጻሕፍቱን ከሜጋ አሳታሚና ማከፋፈያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተወካይ ከአቶ ለማ ሲረከቡ እንደተናገሩት ሜጋ ለተቋሙ የሠጠው መጻሕፍት ለትውልድ እንደተሠጠ የሚቆጠርና ሀገርን የማሻገር ተልዕኮ ያለው ነው፡፡
የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍትና አካዳሚክ ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ግርማ በዚሁ ዕለት መጻሕፍቱን መረከባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *