በሥርዓተ-ፆታ እና የህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተሰጠ፡፡

20/05/2014 ዓ.ም(ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ)
የዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ፍቅርተ ወ/ሥላሴ እንደገለፁት፣ ስልጠናውን በቅድሚያ ለመምህራን መስጠት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የሥርዓተ-ፆታ እና የህይወት ክህሎት አመለካከትን ለራሳቸው በሚገባ ሁኔታ አዳብረው ለተማሪዎቻቸው ለማስረፅ ቅርብ ስለሆኑ ነው፡፡
ከሥርዓተ-ፆታ እና ከህይወት ክህሎት አንፃር በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የቆየ ዘልማዳዊ አስተሳሰብ በሥልጠናው ወቅት በውይይት መልክ ቀርቧል፡፡ በሥልጠናውም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው የወንድንና ሴትን ሚናና ቦታ የመለየት ዘልማዳዊ አስተሳሰብ ከመቅረፍ በተጨማሪ በሥርዓተ-ፆታ እና የህይወት ክህሎት ዙሪያ የመምህራኑን ግንዛቤ የሚያዳብሩ አዳዲስ ሳይንሳዊ ስልቶች እና ስነ-ዘዴዎች ተካተዋል፡፡
ሥልጠናውን የሰጡት ኢንጀንደር ሔልዝ (Engender Health) ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ተቋም የመጡ ባለሙያዎች መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *