በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች የግል (Tuition
Fee-Paying Study Applicant’s
) በመደበኛ ፕሮግራም (Regular እና እረፍት ቀናት (Weekend) በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን
ትምህርታቸውን መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
አመልካቾች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. እውቅና ካለው ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና ከሚያመለክቱበት የትምህርት መስክ ጋር ዝምድና ያለው የት/ት ዝግጅት
ያላቸው፤
2. ከውጭ ሃገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ፤ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ ግምት አሰርተው፤ ለሁለተኛ
ዲግሪ ማመልከት የሚያስችል ማስረጃ በድጋሜ-ምዝገባ እለት ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከድጋሜ ምዝገባ በኋላ ማቅረብ የሚችሉ፤
ማሳሰቢያ
በቅድመ-ምዝገባ ወቅት ምንም አይነት የማመልከቻ ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ዳግም-ምዝገባ እና የመግቢያ ፈተና ጊዜ በማስታወቂያ ሰሌዳ ወይንም በሌሎች የተግባቦት ዘዴዎች የሚገለጽ ሆኖ አመልካቹ/ቿ
በኮሌጁ በአካል መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለድጋሜ-ምዝገባ የተመዘገቡ አመልካቾች በኮሌጁ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
እጩ አመልካቾች በኮሌጁ የሚሰጡ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የመደበኛ (Regular) እና እረፍት ቀናት(Weekend)
ፕሮግራሞችን፤ ከታች ከተያያዘው Online Link ገብተው መመልከት ይችላሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩ አመልካቾች፤ከታች የተጠቀመጠውን የማመልከቻውን ማስፈንጠሪያ( link)
ተጠቅመው ቅድመ-ምዝገባ ማከናወን የሚችሉ እና ተጨማሪ የመመዝግቢያ ፎርም ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
2
ለበለጠ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ድህረ-ገጽ http://www.kmu.edu.et, Facebook ገጽ: https://www.facebook.com/ww.kmu.edu.et
፣ በኮሌጁ ኢሜል አድራሻ: meneilk.hsc@kmu.edu.et ፣ከኮሌጁ ተማሪዎች ቴሌግራም ገጽ፡ KUE Menellik Medical & Health
Science College Student’s channel (link:
https://t.me/kmumhsc በተጨማሪም ከ”ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ
ኮሌጅ ሠራተኞች” ቴሌግራም ገጽ ማግኘት ይችላሉ፡፡
[Access the Online Application Form] https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSczyp-S1h0SFdCcS_qugwS64g3isnhQ3CwKpqiaaZacB65wtA/viewform
[Access the online Downloadable Application Form] https://docs.google.com/document/d/1k1n2SB_QynGG5fLVp3becrBxsCD4ZvuUnDfFRNH1p0o/edit?usp=sharing
የቅድመ-ምዝገባ ማመልከቻ ጊዜ ከመጋቢት 01-07-2014ዓ.ም እስከ መጋቢት 10-07-2014 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ብቻ ማመልከቻ
የምንቀበል ይሆናል፡፡
የትምህርት ክፍያዎች በቀጣይ በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት ይሆናሉ፡፡

ተ.ቁ የክፍያ አይነት የክፍያ ተመን /በብር
1. የማመልከቻ ክፍያ (በመልሶ ምዝገባ) 100
2. የትምህርት ክፍያ በክሬዲት አወር 900
3. የምርምር ክፍያ 10,000

በኮሌጁ የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር

S.No List of Department Modality Duration Of Study /Year
1 Public Health Nutrition Regular
Weekend
2
3


2 Health Service Management Regular
Weekend     
2
3
                                                                                                                  
Posted in Office of the Communication Affairs, Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *