በኮትዩ የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ለዕይታ ቀረበ።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር በመተባበር ያዘጋጇቸውን የኪነ ህንጻና ሌሎች ዲዛይኖች የያዘ ኤግዚቢሽን በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ጂ + 8 ህንጻ ግንቦት 24/2014 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዕይታ አቅርቧል።
የኮትዩ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ሙህዲን ሙሃመድሁሴን ኤግዚቢሽኑን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የትምህርት ትልቁ ጥቅም እውቀትን መያዝ ብቻ ሳይሆን ከትምህርት የተገኘውን እውቀት ወደ ተግባር መለወጥ በመሆኑ፣ በአርክቴክቸር ከመምህራኖቻቸው ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ኤግዚቢሽን በጣም የሚደነቅ እና የሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የከተማ ልማት ጥናት ፋካልቲ ዲን ዶ/ር ይፍሩ ዋቅቶሌ በበኩላቸው፣ ይህ ኤግዚቢሽን በተማሪዎች መዘጋጀቱ ለሚቀጥሉት ተማሪዎች ከፍተኛ ተነሳሽነት የሚፈጥር በመሆኑ፣ በዝግጅቱ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎችን እና መምህራንን አመሰግናለሁ ብለዋል።
የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ዓለምነው ኤግዚቢሽኑ በአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል የመጀመሪያው መሆኑን ገልጸው፤ ተማሪዎቹ በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር ያገኙትን እውቀት አዋህደው ልዩ ልዩ ዲዛይኖችን እና የኪነ ህንፃ ጥበቦችን ለአውዳ-ሪዕዩ ማቅረብ ችለዋል ብለዋል።
የኮትዩ የግንባታና መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ዘሪሁን የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍሉ የዛሬ አምስት አመት ሲከፈት የመጀመሪያ ተቀጣሪ እና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ እንደነበሩ አስታውሰው፣ ትምህርት ክፍሉ ይህን መሰሉን ጥሩ ኤግዚቢሽን የማዘጋጀት ደረጃ ላይ በመድረሱ በጣም ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በኤግዚቢሽኑ ዝግጅት ላይ በመገኘት ተማሪዎቹን ያበረታቱ ሲሆን የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅ ተማሪዎች ያቀረቧቸውን የኪነ ህንፃ ንድፍ ስራዎቻቸውን በተግበር መሬት ላይ በማሳረፍ አሻራዎቻቸውን ለሚቀጥለው ትውልድ መተው እንዲችሉ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ የግንባታ ቦታ እንደሚያመቻቹላቸው ቃል ገብተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ተማሪዎች የንድፍ ስራዎቻቸው ውጤት ያሆነውን ስጦታ ለፕሬዝዳንቱ አበርክተዋል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ ልዩ ልዩ የኪነ ህንፃ ዲዛይኖች፣ የጥበብ ቅቦች እና ምስሎች የቀረቡ ሲሆን፣ እነዚህ ሥራዎችም በተሳታፊዎች ተጎብኝተዋል።
                            የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 4 people and indoor
May be an image of 9 people, people standing and indoor
May be an image of 14 people, people standing and indoor
May be an image of 11 people, people standing and indoor
May be an image of 1 person, sitting and standing
No photo description available.
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *