የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁራን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ውይይት መነሻ የሚሆኑ በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አቀረቡ።

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ ምሁራን የተዘጋጁ እና በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ቀርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደረገባቸው።
የማኅበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ ዲን ዶ/ር ግርማ በላቸው ለጉባዔው ተሳታፊዎች ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት፤ የማኅበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ አገራዊ፣ ወቅታዊና አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የፋካልቲው ምሁራን ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሑፎች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት፤ እንደዩኒቨርሲቲ ምሁር በእነዚህ ወቅታዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መወያየት ለሃገር ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ ሃገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሳትፈልግ በገባችበት ጦርነት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መድረሳቸውን ተናግረዋል። መነሻ ጽሑፎች የሃገራችንን ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚጠቁሙ ከመሆናቸውም ባሻገር በጦርነቱ ወቅት የወደሙ ቁሶችን በምን መልኩ እንደሚተኩ እና ከጦርነቱ በኋላ ራሳችንን እንዴት አረጋግተን ወደፊት መቀጠል እንችላለን የሚሉት ሀሳቦች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ዶ/ር ሽመልስ አያይዘውም፣ ሃገርን ከውጪ ከሚመጣ ጠላት መከላከል ብቻ ሳይሆን በሃገር ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን እንዴት አድርጎ ማስቀረት እንደሚቻል በሚያስገነዝቡ ውይይቶች ላይ መሳተፍ እንደግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደሃገርም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።ዶ/ር አየነው ብርሃኑ “ድህረ ግጭት የሠላም ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ እንዲሁም ዶ/ር አልማው ክፍሌ “የሃገር ፍቅርና የሃገር ግንባታ ትስስር በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ሐሳብ አቅርበዋል። የጉባዔው ተሳታፊዎችም በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን፣ የጽሁፎቹ አቅራቢዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 1 person and indoorMay be an image of 1 person and indoorMay be an image of 2 people, people sitting and indoorMay be an image of 4 people, people sitting and indoor
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *