በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በስታትስቲክስ የትምህርት መስክ የሦስተኛ ዲግሪ (Ph.D) የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የአፕል ችግኝ ተከሉ፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በስታትስቲክስ የትምህርት መስክ የሦስተኛ ዲግሪ (Ph.D) የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የአፕል ችግኝ ተክለዋል፡፡ በዚሁ ወቅት የአካዳሚክ ጉዳዮች ጊ/ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር ሽመልስ ዘውዴ እንደተናገሩት፣ ይህ አይነቱ የችግኝ ተከላ ተግባር ከፒ. ኤች.ዲ ተማሪዎች የሚጠበቅ መልካም አርአያነት መሆኑን በመጥቀስ፣ የአፕል ፍሬው እስኪደርስ ድረስ ተማሪዎቹ በግቢው ውስጥ ሊቆዩ ስለሚችሉ ተንከባክበው ለፍሬ ማብቃት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
የችግኝ ተከላው ስነስርዓት በተካሄደበት ውቅት በስታትስቲክስ የትምህርት መስክ የሦስተኛ ዲግሪ መርሐግብር የተማሪዎቹ መምህር የሆኑት ዶ/ር አየለ ታዬ እንዳሉት ተማሪዎቹ ቀደም ሲል በእንጦጦ አካባቢ ችግኝ መትከላቸውን አስታውሰው በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢም ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ማከናወናቸው በምሳሌነት የሚታይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የችግኝ መትከያ ቦታውን ስለፈቀደላቸውም አመስግነዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከመምህራቸው ጋር በመሆን የተከሉትን 15 የአፕል ችግኝ ለሦስት ሺህ ብር በላይ በማውጣት በራሳቸው ወጪ የገዙ ሲሆን፣ የችግኝ ተከላውን ሂደትም የፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምስ አባተ ከተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች ጋር በመተባበር ያመቻቹ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
                             የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 10 people, people standing, tree and sky
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *