በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

ጥብቅ ማስታወቂያ

                                            **************

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

ውድ ተፈታኞች በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ወደ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ መያዝ የተፈቀደላችሁ ቁሳቁሶች ብቻ ይዛችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሰስባለን፡፡

    1. ተፈታኞች እንዲይዙ የተፈቀደላቸው ቁሳቁሶች

Ø መጻሕፍት እና ሲያጠናቿው የነበሩ ማስታወሻዎች

Ø ልብስ የሌሊት፤ ልብሶችን ጨምሮ (አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ የመሳሰሉት)፣

Ø የመፈተኛ ካርድ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ

Ø የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ… የመሳሰሉት)

Ø ገንዘብ (ብር)

Ø ደረቅ ምግብ ብቻ ናቸው፡፡

    1. ተፈታኞች እንዳይዙ የተከለከሉ ቁሳቁሶች

Ø ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ (ቪዲዮ፣ የፎቶራፍ ካሜራ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላብቶፕ፣ስልክ፣ አይፖድ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ፍላሽ፤ ማጂክ ጃኬት እና የመሳሰሉት) ናቸው፡፡

Ø ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ማንኛውም ቀለበት፣ ማንኛውም ጌጥ፣ ሰዓት፣ ሃብል፣ የጸጉር ጌጥ ወዘተ

Ø መነፅር (ከዕይታ ችግር ጋር በተያያዘ በሃኪም የተፈቀደ ካልሆነ በስተቀር)

Ø የሃኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት

III. ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ወቅት የሚጠበቁባቸው ተግባራት

Ø ማንኛውም ተፈታኝ የዩኒቨርሲቲውን ሕግና ደንብ ተከትሎ የፈተናውን ጊዜ ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ የፈተና ህግና ደንቦችን በአግባቡ ማክበር ይጠበቅበታል፡፡

Ø ማንኛውም ተማሪ ከሌሎች ተፈታኞች ጋር በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ በሰላም የፈተናውን ጊዜ ማሳለፍ ይኖርበታል፡፡

Ø ማንኛውም ተማሪ በፈተና ጊዜ ካልሆነ በስተቀር ወደ መፈተኛ ክፍሎች መግባት አይኖርበትም፡፡ ከፈተና ሰዓት ውጪ ተፈታኞች ከማደሪያ ክፍሎቻችው ወይም ከተፈቀዱላቸው ሌሎች አካባቢዎች ውጪ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ የመመገቢያ እና የፈተና ሰዓትን በአግባቡ ማክበር ይኖርበታል፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጠጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት አይችልም፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ በፈተና ሰዓት፣ በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም አይችልም፡፡

Ø የማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ወላጆች፣ አሳዳጊዎችም ሆኑ ሌላ ቤተሰብ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድም፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ፣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ የመገኛት ግዴታ አለበት ፡፡

Ø ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት፡፡

                                                                                                    ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *