የ2015 ትምህርት ዘመን የነባር የድህረ-ምረቃ፣ መጀመሪያ ዲግሪና የዲፕሎማ የቀን፣የማታና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች (ከ2ኛ አመት ድህረምረቃ ፕሮግራም በስተቀር) የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ከጥቅምት 28 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወን መሆኑን እያስታወቅን በተጠቀሱት ቀናት ‘’online’’ ምዝገባ እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ
-
- የድህረ-ምረቃና የ “Extension” ተማሪዎች የምዝገባ ክፍያ ስርአት ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በ online CBE Birr መሆኑን፣ በደረሰኝና በባንክ አካውንት የማናስተናግድና በደረሰኝና በባንክ አካውንት ለምዝገባ የተከፈለ ክፍያ ተቀባይነት የማይኖረው መሆኑን
- ከምዝገባ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የቀድሞው የተማሪዎች መታወቂያ የሚቀየር ስለሆነ በሲስተሙ ፕሮፋይላችሁ ላይ ለመታወቂያ የሚሆን ፎቶ ግራፍ(3 ×4) ከወዲሁ እንድታስገቡና ከየኮሌጁ/ፋካሊቲ/አካዳሚ በመጠየቅ መታወቂያችሁን እንድታስቀይሩ
- የ2015 ትምህርት አንደኛ ሴሚስተር ትምህርት ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት