ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለው ጠንካራ ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ዛሬ ነሀሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ተቋሙ እያካሄዳቸው ያላቸውን የመሠረተ ልማት አውታሮች እና ዩኒቨርሲቲውን የማቋቋም ሥራ ያለበትን ጎብኝተዋል፡፡ለማህበረሰብ ተወካዮቹ በተደረገው ማስጎብኘት ገለጻ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ሲሆኑ በገለጻቸውም ተቋሙን ቀደም ስንቀበል ከማንም በላይ የያኔው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የነበረበትን ደረጃ ታስታውሳላችሁ አሁን ካለበትም ለማነፃፀር ትክክለኛ ዓይን የናንተ ነው፤ ፍፁም ተረስቶ ብቻ ሳይሆን ተትቶ የቆየ ሲሆን አሁን በለውጡ በመልሶ ማደራጀት የሀገሪቱ ብቸኛ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ሲታወጅ ከአባባል ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን መሠረተልማት የሚመጥን ለማድረግ መንግስት ፕሮጀክቶችን ፈቅዶ ለተልዕኮው የሚመጥን እንዲሆን በሙሉ ቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን። በመሆኑም ሥራችንን ለማየትና ከወዲሁ አስተያየታችሁን ልትለግሱን የህብረተሰቡን አስተያየት ይዛችሁ ልትጎበኙን በመምጣታችሁ ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።አያይዘውም በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን ለተሰጠው ተልዕኮ ምቹ፣ በተማሪዎች ተመራጭ እና ተወዳዳሪ የሚያደርጉት የመሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች እየተገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ብርሃነመስቀል፣ ግንባታዎቹ ሲጠናቀቁ ለተልዕኮው መወጣት ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን የምትረዱት ሆኖ በተጓዳኝ ለአካባቢው መልካም ገጽታን ከማላበስና አካባቢውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛነት አብራርተውላቸዋል ።የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ወንድሙ ግዛው በበኩላቸውበሁሉ ክልል መሠረት እየተጣለ አንድ ተብሎ ዩኒቨርሲቲ ሲገነባ ይሄኛው ስንቱን መምህር እያስተማረ ለሀገር ያበረከተ ተቋም ለምን በቀደመው ሥርዓት ተጥሎ እንደቆየ ሁሌ ስናዝን የኖርን ሲሆን በለውጡ እና ይህ አሁን ያለው አመራር ከመጣ የታየው ለውጥ የሚደነቅ ነው ያሉት ተወካዩ እንቅስቃሴያችሁን እና የየተቋሙን የየዕለት ተዕለት ለውጥ ማህበረሰቡ በቅርበት እንደሚከታተልና በዚህም ለዩኒቨርሲቲው አመራር ከፍተኛ ከበረታ እንዳለው አስረድተዋል።አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት ቤቶችን በማገዝና በማዘመን ፣ ለአከባቢው አልፎ ተርፎም ለከተማው ወጣቶች የተለያዩ ሙያዊ ሥልጠናዎችን በመስጠት በተለይም በባህሪይ እነፃ እያደረገ ያለው ሥራ ፣ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ተግባራት ለአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ላለው ድጋፍና እገዛዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በጉብኝታቸው በተመለከቱት ነገር መደነቃቸውንና ዩኒቨርሲቲው እየተጓዘበት ባለው ከፍተኛ ተቋማዊ እድገት መደሰታቸውን ገልጸው፣ ማንኛውንም እገዛ ለማድረግ እንደሁልጊዜው ከተቋሙ ጎን እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል ፡፡
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *