ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መካከለኛ አመራሮችን በአዲስ መልኩ ማደራጀቱን አስታወቀ፡፡

መስከረም 08፣2014
ዩኒቨርሲቲው በአዲስ መልክ በሜትሮፖሊታን ደረጃ ከተዋቀረ ጀምሮ፣ በለውጥ ጎዳና እንዲጓዝ ካስቻላቸው ዋነኛው ስራዎች መካከል የአመራሮች አደረጃጀት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በዚህም መሠረት፣ ዩኒቨርሲቲውን ባለፉት አመታት ሲመሩ የነበሩና ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት መካከለኛ አመራሮች የምስጋና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን፣ በምትካቸውም አዳዲስ አመራሮች ተመድበዋል፡፡
በርክክብ መርኃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እንደገለፁት ምደባው በውድድር እንደነበረና ምሳሌ ሊሆን በሚችል መልኩ የተከናወነ ሲሆን በርካታ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበታል። ምርጫውም
ልምድን ፣ ለሥራ ያላቸውን ተነሳሽነትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ነበር። ምደባው ለውጥን ማዕከል አድርጎ አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት እንዲመጡ ያስቻለ ነው። በዚህም አዲሱ አመራር ዩኒቨርሲቲውን አሁን ከደረሰበት ደረጃ ከፍ ወዳለ ደረጃ ሊያሸጋግሩ ይችላሉ ተብለው እምነት ተጥሎባቸዋል ። በአዲስ አደራን የተቀበሉት እነዚህ አመራሮች ወደሥራ ከመግባታቸው በፊት የአመራርነት (Leadership) ሥልጠና እንደሚሠጣቸው ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል ።

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *