ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ንቅናቄ ዘመቻን በይፋ አስጀመረ፡፡

የእናት ሀገሩ ጡት ነካሽ የሆነው ጁንታ በፈጠረው ችግር ምክንያት የምዕራባዊያንን እውነታውን ያላገናዘበ ፍርደ-ገምድል ውሳኔን በመቋወም ዜጎች ሀሳባቸውን እየገለፁበት ከሚገኙበት መንገድ አንዱ የሆነውን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ንቅናቄ ዘመቻን ሁሉም የዩኒቨርሰቲ ማህበረሰብ በተገኙበት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በዚህ የንቅናቄ ዘመቻ ላይ አሻራቸውን ለማኖር ለተገኙ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች ፕሬዝዳንቱ የዘመቻውን ዓለማ ሲያስረዱ የምዕራቡ ዓለም በተዛባ አመለካከት በኢትዮጵያ ላይ እያደረገ ያለውን ጫና ከመቋወም በዘለለ ንቅናቄው ትክክለኛ መረጃንም መስጨበጥ አላማው እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዜጎች ከዚህ በፊት በእንዲህ አይነት ሁኔታ በነቂስ ወጥተው በአንድ ድምፅ የተቃውሞ መልዕክታቸውን በቀጥታ ለነጩ ቤተ-መንግስት ሲልኩ በታሪክ የመጀመሪያ እንደሆነ አስረድተው ይህ ንቅናቄ ምዕራባዊያን ትክክለኛ መረጃ አግኝተው ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉ እንደሚረዳቸው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
የዩኒቨርሰቲ ማህበረሰብም ይህንን ዓላማ ተገንዝቦ በመርሀ-ግብሩ ላይ በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉና ሀገራቸውን ከሴራ የመከላከል ዘመቻው አካል እንዲሆኑ መልዕክታቸውን ከስተላለፉ በኃላ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና በንቅናቄው ዘመቻ መልዕክታቸውን በፊርማቸው በነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተ-መንግሥት በማስተላለፍ ንቅናቄውን አስጀምረዋል። መላው የዩኒቨርሰቲው ማህበረሰብም ፊርማውን በማኖር “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ንቅናቄ ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል፡፡
መስከረም 14/2014
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት
Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *