ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሩ የስራ የአመራር ክህሎት ማጠናከሪያ ስልጠና ሠጠ፡፡

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በውድድር ወደ አመራርነት ደረጃ ላደጉና ለነባሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩ መስከረም 19 እና 20/2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው መድረክ የስራ የአመራር ክህሎት ማጠናከሪያ ስልጠና ሠጠ፡፡ የተከበሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በስልጠናው መክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ስልጠናው የመሪዎቹን የአመራር ብቃትና በማሳድግ ብቁ መሪዎችን ለመፍጠር ታቅዶ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ላይ ያሉ እና የካበተ ተሞክሮ እና ልምድ ያላቸው መሪዎችንና ምሁራንን በመጋበዝ ሳይንሳዊ የአመራር ዕውቀትን ለዘመናት ካካበቱት ዕውቀታቸውና የህይወት ተመክሮአቸው በማቀናጀት እንዲያካፍሉ በተመረጡ ባለሙያዎች እንዲሠጥ መደረጉን ኘሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ስልጠናው በክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ፣ በክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በራሳቸው በዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ፣ በዶ/ር ወርቁ ፣ በፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ እና በዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ በተለያዩ 6 ለአመራርነት ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሠጠ ነው። ዓላማውም አመራር የመሪነት ኃላፊነቱን እንደተረከበ በማብቂያ እና ማነቃቂያ ሥልጠና ወደሥራ በማስገባት አመራሩንም ተቋሙንም ውጤታማ ማድረግ መቻል ነው።
Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *