ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ የሽግግር ሂዳትን አስመልክቶ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

                                                                                                                                                                            17/03/2014 ዓ.ም
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት በዋና ግቢው የተቋሙን ሽግግር ሂዳት አስመልክቶ ጥልቅ ውይይት አካሄዷል፡፡ በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና የተቋሙ ታሪካዊ ዳራና ችግሮቹ እንዲሁም የወደፊት ትኩረት አቅጣጫዎቹ ላይ በማተኮር ለውይይት መነሻ የሚሆን ገላጭ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የትምህርት ልህቀት፣ የምርምር ስርፀት፣ የዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ፣ መልካም አስተዳደራዊና የስራ አመራር ለውጥ፣ ማህበረሰባዊ ተሳትፎን ማሳደግ፣ ገበያ-መር በሆነ መልክ የተቋሙን ፕሮግራሞች በመቃኘትና በአዋጅ 1263/2014 የተሰጠውን የትምህርት ዩኒቨርሲቲነትን ተልዕኮ በብቃት መወጣት የተቋሙ የወደፊት የትኩራት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለሀገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት ምክንያቶቹና ለችግሮቹ መፍትሄ ናቸው ብለው ያሉዋቸውን ቁምነገሮች ከዘረዘሩ በኋላ የስራ መመሪያና የዩኒቨርሲቲውን የወደፊት ትኩረት አቅጣጫ ሲያመላክቱ እንደተናገሩት እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በኃላፊነትና በተቆርቋሪነት ለዩኒቨርሲቲው አዲስ በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ ምክክር ላይ በንቃት በመሳተፍ በአገራችን የትምህርት ጥራት ለውጥ እንዲመጣ በትጋት በመስራት ልዩ አስተዋፅኦ ማበርከት ከዩኒቨርሲቲው እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መንግስት ከዩኒቨርሲቲው የሚጠብቀው ለውጥ፣ ጥገናዊ ሳይሆን መሠረታዊ ለውጥ እንደሆነ አስምሮበት ለዚሁ ተልዕኮ ዩኒቨርሲቲው ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት አሳስቧል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
 
Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *