በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች የግል
(
Tuition Fee-Paying Study Applicant’s) በመደበኛ ፕሮግራም (ጀነሪክ እና ፖስት ቤዚክ) እና በድህረ ምረቃ ፕሮግራም በመደበኛ
እና በእረፍት ቀናት በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር
ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
አመልካቾች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ እና ቅድመ-ምዝገባ ወቅት የትምህርት ሚንስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳወቀውን የመቁረጫ
ነጥብ ማሟላታቸው፤ የተረጋገጠ እና ማሟላት የሚችሉ፤ [ለ አራት አመት ፕሮግራም (Generic Program].
2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር በአዲሱ
የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 ወይንም በቀድሞው 10+3 ወይንም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት
ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የአንድ ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው
መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በድጋሜ-ምዝገባ እለት ማቅረብ የሚችሉ፤ [ለ ፖስት ቤዚክ ፕሮግራም (Post Basic
Program) ].
3. ከውጭ ሃገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው አመልካቾች ከሆኑ፤ ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ
ግምት አሰርተው፤ ለመጀመሪያ ዲግሪ ማመልከት ያሚያስችል ማስረጃ በድጋሜ-ምዝገባ እለት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. ለድጋሜ-ምዝገባ የተመዘገቡ አመልካቾች በኮሌጁ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች መውሰድ እና ማለፍ የሚጠበቅባቸው
ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ
በቅድመ-ምዝጋባ ወቅት ምንም አይነት የማመልከቻ ክፍያ የማይጠየቅ መሆኑን እናሳውቃለን፡
ዳግም-ምዝገባ የሚከናወነው፤ የ2014ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል ትምህርት ሚንስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳወቀውን የማለፊያ
ነጥብ ከተገለጸ በኋላ በኮሌጁ በአካል በመገኘት ይሆናል፡፡
እጩ አመልካቾች በኮሌጁ የሚሰጡ መደበኛ ፕሮግራም የጀነሪክ እና ፖስት ቤዚክ መደበኛ ፕሮግራሞችን ፤ ከታች
ከተያያዘው የጎግል ፎርም ሊንክ ገብተው ማየት ይችላሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩ አመልካቾች፤ከታች የተጠቀመጠውን የማመልከቻውን ማስፈንጠሪያ(
link) ተጠቅመው ቅድመ ምዝገባ ማከናወን የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ድህረ-ገጽ http://www.kmu.edu.et, Facebook ገጽ:
https://www.facebook.com/ww.kmu.edu.et ፣ በኮሌጁ ኢሜል አድራሻ: meneilk.hsc@kmu.edu.et ፣ከኮሌጁ
ተማሪዎች ቴሌግራም ገጽ፡ KUE Menellik Medical & Health Science College Student’s channel (link:
https://t.me/kmumhsc በተጨማሪም ከ”ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሠራተኞች” ቴሌግራም ገጽ
ማግኘት ይችላሉ፡፡
[Access the Online Application Form] https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfwoA2iMYqKoSSPWzK6vR5K45GGEELZaL9fL5m6TMB4xV9-4Q/viewform
[Access the online Downloadable Application Form] https://docs.google.com/document/d/1GSJ2_24BiLq8SMYVsrTGKUVtX5zps-jRiFCA0JX5Rk8/edit?usp=sharing
የቅድመ-ምዝገባ ማመልከቻ ጊዜ ከመጋቢት 01-07-2014ዓ.ም እስከ መጋቢት 10-07-2014 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ብቻ
ማመልከቻ የምንቀበል ይሆናል፡፡
ለግንዛቤ
በጤና ሚኒስቴር የጤና ባለሙያዎቸ ብቃት ምዘናና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት በሚሰጠው የብቃት ምዘና ፤የኮሌጁ ተማሪዎች
በአማካኝ መጠነ-ማለፍ
(Pass Rate) ከ 95% በላይ ፤ ያስመዘገበ መሆኑ፤ ተቋሙን ተመራጭ ያደርገዋል፡፡
ኮሌጁ ማሀበረሰቡን ማገልገል አላማው በመሆኑ፤ ከተማሪዎችና ወላጆች የሚጠይቀው ከመማር ማስተማር ወጪ ውስጥ የትምህርት
ወጪ ብቻ መሆኑ፤
ዋና ዋና የትምህርት ክፍያዎች በቀጣይ በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት ይሆናሉ፡፡


ተ.ቁ የክፍያ አይነት የክፍያ ተመን
1. የማመልከቻ ክፍያ (በመልሶ ምዝገባ) 100
2. የትምህርት ክፍያ በክሬዲት ለቲዎሪ አወር 95
3. ለሰርቶ ማሳያ፣ ተግባር ልምምድ በክሬዲት አወር 63.33

በኮሌጁ የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር

S.NO LIST OF DEPARTMENT MODALITY DURATION OF STUDY /YEAR
1 Nursing Generic 4
Post basic 2/1/2
2 Medical Laboratory Science Generic 4
Post basic 2/1/2
3 Medical Radiology Technology Generic 4
Post basic 2/1/2
4 Pharmacy Generic 5
Post Basic 3
5 Psychiatry Nursing Generic 4
Post Basic 2/1/2
6 Midwifery Generic 4
Post Basic 2/1/2

 

7 Human Nutrition Generic 4
8 Health Informatics Post Basic 2/1/2
9 Family Health Post basic 2/1/2
10 Emergency and Critical Care Nursing Post basic 2/1/2
11 Surgical Nursing Post basic 2/1/2
12 Pediatrics and Child Health Nursing Post basic 2/1/2
13 Neonatal Nursing Post basic 2/1/2
14 Operative Theater Nursing Post basic 2/1/2
15 Anesthesia

Post basic

Generic

3

4

 

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *