የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ሎጎ በይፋ ተመረቀ።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ዓርማ (ሎጎ) ዛሬ ሰኔ 15/2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሕንጻ በተዘጋጀ ሥነስርዓት በይፋ ተመርቋል።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲን አዲሱን ሎጎ በይፋ የመረቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና በሥነስርዓቱ ላይ ዩኒቨርሲቲ ው በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ዓርማው ዩኒቨርሲቲው ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያመለክት ሲሆን፣ በዓርማው ላይ የሰፈሩት የደረጃ ምልክቶች ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ አሁን የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወደኋላ የማይመለስ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። በተጨማሪም፣ የመፅሐፉ እና የዲግሪው ቆብ ምልክቶች የትምህርት በመሆናቸው ተማሪዎች መጽሐፉን በበቂ አገላብጠው ጨርሰው ሲመረቁና ዲግሪያቸውን ሲይዙ ለዓለም ብርሃን እንደሚሆኑ በፀሐይ ብርሃን የተመሰሉ መሆኑን ዶክተር ብርሃነመስቀል አብራርተዋል።
በዛሬው ዕለት በይፋ ከተመረቀው አዲሱ ሎጎ በተጨማሪ፣ የዩኒቨርሲቲው መዝሙር በአዲስ መልክ ተሰርቶ መጠናቀቁን ዶክተር ብርሃነመስቀል ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም የዩኒቨርሲቲውን ፍኖተ ካርታ ፣ ካሪኩለም ማዕቀፍ እና መዋቅር ጨምሮ በርካታ አስተዳደራዊ እና በጀት ነክ ጉዳዮች በፍጥነት እየተሰሩ መሆናቸውን እና የአራት አዳዲስ ህንፃዎች ግንባታም መጀመሩን ተናግረዋል።
በመጨረሻም እኛ አላፊዎች መሆናችንን ባለመዘንጋት እጅ ለእጅ ተያይዘን በታርክ የምንታወስበትን ተሻጋሪ ሥራ ለትውልድ እንስራ በማለት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሎጎውም ከሰኔ 16 /2014 ጀምሮ በይፋ የዱሮውን ተክቶ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ።
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 5 people, people standing and outdoors
May be an image of 7 people, people sitting and people standing
May be an image of 1 person
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *