ኮትዩ የኤች. አይቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዩኒቨርስቲው ለሚያሳድጋቸው ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የኤች. አይቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዩኒቨርሲቲው ለሚያሳድጋቸው የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች ወርሃዊ ወጪያቸውን መሸፈኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግምታቸው ከአንድ መቶ ሺህ የሚበልጥ ዓመታዊ የትምህርት መሣሪዎች ማለትም ልዩ ልዩ አልባሳት እና የትምህርት ቁሳቁስ ስጦታ አበርክቷል።
የኮተቤ የትምህርት የኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በድጋፍ ሥነስርዓቱ ላይ እንደገለፁት፣ የዩኒቨርሲቲው እገዛ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ መታየት እንዳለበት ጠቅሰው፣ በቀጣይም ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ የተማሪዎቹ ወላጆችም ልጆቻቸው ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ በመምከር ለቁምነገር እንዲያበቁዋቸው አሳስበዋል። አያይዘውም፣ በትምህርታቸው ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎች እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የሚዘልቅ እገዛ እንደሚደረግ አበረታትተዋቸዋል።
የኮተቤ የትምህርት የኒቨርሲቲ የኤች. አይቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ ምኞት ጌታቸው በበኩላቸው፣ በዳይሬክቶሬቱ ስር የተቋቋመው የኤች.አይቪ. ፈንድ ለህጻናቱ ድጋፍ የሚውለውን ገቢ የሚያገኘው የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ከወርሃዊ ደሞዛቸው ላይ ለዚሁ ዓላማ ከሚያደርጉት መዋጮ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ለ2015 ዓ.ም ትምህርታቸው የሚገለገሉበት የትምህርት ቤት ቦርሳ፣ ሙሉ ልብስ፣ ፒጃማ፣ ቱታ፣ ለትምህርት ቤት የሚሆን ጫማ፣ ነጠላ ጫማ፣ እና ለክረምት ወቅት የሚሆኑ ሌሎች አልባሳትን አስራ ሰባት ለሚሆኑ ህጻናት አስረክቧል። ከአስራ ሰባቱ ተማሪዎች በተጨማሪ ሁለት ተማሪዎች የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ ህንድ ሀገር መሄዳቸው በሥነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ድጋፍ ከተደረገላቸው ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቤተልሄም በቀለ እና ተማሪ ተገኑ ደርጉ “ኮተቤ የትምህርት የኒቨርሲቲ የሚያደርግልን ድጋፍ በትምህርታችን ውጤታማ እንድንሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
         የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 10 people, child, people sitting, people standing and indoorMay be an image of 16 people, child, people sitting, people standing and indoorMay be an image of 10 people, people sitting, people standing and indoorMay be an image of 1 person and indoorMay be an image of 3 people, child, people standing and indoor
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *