አዲሱ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ዩኒቨርሲቲውን ጎበኙ፡፡

አዲሱ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት በ30/10/2014 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው የስራ አመራሮች ጋር ትውውቅ ካደረጉ በኋላ በዋናው ግቢ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ አዳዲስ ግንባታዎችን፣ ቤተ መጻሕፍትና ሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ስራ የአመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ አዲሱ ቦርድ አባላት ከፍተኛ የሥራ ልምድ ያላቸው በመሆኑ በለውጥ ሂደት ላይ የሚገኘውን የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ወደ ላቀ የዕደገት እና የታሪክ ምዕራፍ የማሸጋገር ታሪካዊ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና በበኩላቸው አዲሱ የስራ የአመራር ቦርድ አባላት ፕሮፋይል ከፍተኛ ከመሆኑም በተጨማሪ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ያላቸው በመሆኑ ለዩኒቨርሲቲው ዕድገት እንደ ምቹ ሁኔታ የሚታይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድም ሆነ በዩኒቨርሲተው ሁለንተናዊ ዕድገት ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራሮች በአዲስ መልክ ከተዋቀረው የቦርድ አባላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
የቦርዱ አባላት የዩኒቨርሲቲው የሽግግር ሂደት፣ የመዋቅር ሰነድ እንዲሁም የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ገለፃ ከተደረገላቸው በኋላ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ የአዲሱ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ የተከበሩ አቶ መለስ አለሙ ምክትል ሰብሳቢ፣ የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ጸሐፊ፣ ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቅ አባል፣ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ አባል፣ አምባሣደር ብርቱካን አያኖ አባል፣ ዶ/ር ተመቸኝ እንግዳ አባል እና ዶ/ር ወንድወሰን ታምራት አባል መሆናቸው ታውቋል፡፡
                                                          የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
 
 
 
 
 
May be an image of 4 people, people standing and outdoors
May be an image of 10 people, people standing, tree and outdoors
May be an image of 9 people, people standing, suit and indoor
Posted in Office of the Communication Affairs, Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *