የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የበጎ ፈቃደኝነት ቀን የሆነውን ጳጉሜ አንድ ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተከሉ፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የበጎ ፈቃደኝነት ቀን ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በተዘጋጁ ስፍራዎች ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ፍራፍሬ ችግኞችን ጭምር ዛሬ ጳጉሜ 1/2014 ዓ.ም ተክለዋል፡፡
የችግኝ ተከላው ስነስርዓት በተጀመረበት ወቅት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ ጳጉሜ አንድ ቀን የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በመሆኑ ወደን ፈቅደን የምንሰራበት፣ ወደን ፈቅደን ችግኝ የምንተክልበት፣ ወደን ፈቅደን ሀገራችንን ከወራሪው ኃይል የምንከላከልበት ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል፡፡ ወንድሞቻችን የመከላከያ ሠራዊት አባላት በግንባር እየተፋለሙ እና ለሀገራቸው የህይወት መስዋዕት እየከፈሉ መሆናቸውን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፣ እኛ ደግሞ በአንድ በኩል ልማቱን እያሳለጥን በሌላ በኩል ለሀገር መከላከሉ ደጀንነታችንን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል።
ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ከተንከባከብነው ለትውልድ የሚተላለፍ፣ ድርቅን በመከላከል የሀገራችን ምህዳር የተሻለ የሚያደርግ ጠቀሜታውም ዘርፈ ብዙ ነው ያሉት
ዶ/ር ብርሃነመስቀል አያይዘው የወለደችንና ያሳደገችን እናት ሀገራችን ለኛ ችግኛችን ናት ልንጠብቃት ልንንከባከባት ይገባል ለዚህም በዚህ አጋጣሚ በግንባር ሆኖ መስዋዕትነት እየከፈለ ካለው መከላከያችን ጎን መሆናችንንና ለሚጠበቅብን ሁሉ አለኝታችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የግቢ ውበት እና መናፈሻ ሥራ ኃላፊ አቶ ግርማ ከፍያለው በዚሁ ጊዜ ስለ ችግኝ አተካከል ገለፃ የሰጡ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት የተተከሉትን 600 ችግኞች ጨምሮ በዘንድሮው ዓመት 18 ሺህ ልዩ ልዩ ችግኞች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ መተከላቸውን ተናግረዋል፡፡
ከተተከሉት ችግኞች መካከል ጓሳ የተሰኘ የሣር ዝርያን ጨምሮ አፕል (ፖም)፣ አቦካዶ፣ ፅድ፣ አልተርናታ፣ ሳይፕረስ እና ስፓቶዲያ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
                                     ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 6 people, people standing, tree and grassMay be an image of 5 people, people standing and outdoors
Posted in Office of the Communication Affairs, Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *