በዓለም ዓቅፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን የኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች መጠቀም የሚያስችል ውል ተቋሙ ስለመግባቱና ስለአጠቃቀሙ ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ገለፃ ተሰጠ፡፡

በዓለም ዓቅፍ ደረጃ እውቅና እና ጥራት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች መጠቀም የሚያስችል የማስተዋወቅ ገለፃ በ12/01/2015 ዓ.ም በተሰጠበት ወቅት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ እንዳሉት፣ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በአዲስ ስያሜና በአዲስ ተልዕኮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ምርምር ዋናው የዩኒቨርሲቲው ትኩረት ስለሆነም በተለያዩ ሀገራት፣ በተለያዩ አውዶች የተሰሩትን ምርምሮች ማንበብ፣ መተንተንና መጠቀም ስለሚያስፈልግ አሁን ባለንበት ዓለም ውስጥ ጥራትና እውቅና ያላቸውን የኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች መግኘት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጉልህ ሚና እንዳለው አፅዕኖት ሰጥተው በመናገር ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍትና አካዳሚክ ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረመስቀል ግርማ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኑን ከሚመሰክሩት ተግባራት መካከል ለጥናት እና ምርምር አጋዥ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት እና መጠቀም የሚያስችል ስልትን ማመቻቸት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላቅ ያለ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡
ውል የተገባባቸው የኤሌክትሮኒክ ጆርናሎች ለማስተዋወቅና ገለፃ ለመስጠት ከአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የመጡት ባለሙያዎች፣ ዶክተር መልካሙ በየነ እና አቶ ጌትነት ለማ ጆርናሎቹ በዓለም ዓቅፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውና ለመማር-ማስተማር እንዲሁም ለምርምር ስራዎች እጅግ የጎላ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
                                        ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of 3 people, people sitting and indoor
May be an image of 3 people, people sitting and people standingMay be an image of 5 people, people sitting and indoor
May be an image of 6 people and people sitting
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *