ማስታወቂያ ! ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

የ2015 ትምህርት ዘመን የነባር የድህረ-ምረቃ፣ መጀመሪያ ዲግሪና የዲፕሎማ  የቀን፣የማታና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች (ከ2ኛ አመት ድህረምረቃ ፕሮግራም በስተቀር) የአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ  ከጥቅምት 28 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወን መሆኑን እያስታወቅን በተጠቀሱት ቀናት ‘’online’’ ምዝገባ እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ

    • የድህረ-ምረቃና የ “Extension” ተማሪዎች የምዝገባ ክፍያ ስርአት ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በ online  CBE Birr  መሆኑን፣  በደረሰኝና በባንክ አካውንት የማናስተናግድና  በደረሰኝና በባንክ አካውንት ለምዝገባ የተከፈለ ክፍያ ተቀባይነት የማይኖረው መሆኑን
    • ከምዝገባ በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የቀድሞው የተማሪዎች መታወቂያ የሚቀየር ስለሆነ በሲስተሙ ፕሮፋይላችሁ ላይ ለመታወቂያ የሚሆን ፎቶ ግራፍ(3 ×4) ከወዲሁ እንድታስገቡና ከየኮሌጁ/ፋካሊቲ/አካዳሚ በመጠየቅ መታወቂያችሁን እንድታስቀይሩ
    • የ2015 ትምህርት አንደኛ ሴሚስተር ትምህርት  ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

Posted in Uncategorized.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *