የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ እንደቀድሞው ሁሉ ዘንድሮም በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች የላቀ ውጤት አስመዝግቧል ።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ2016 ዓ.ም ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉንም (100%) በከፍተኛ ውጤት ማሳለፍ መቻላችንን ስናበስር እጅግ ደስ እያለን ነው።የተመዘገበው ውጤት ተማሪዎችን ከታች ይዞ መኮትኮት ከተቻለ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው።የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በአዲስ አበባ ከተማ ከ8ኛ ክፍል ወደ 9ኛ የሚሸጋገሩ ተማሪዎችን በመቀበል በዩኒቨርስቲው የበላይ አመራር ልዩ ክትትልና ድጋፍ ፤ ለዚሁ ተልዕኮ በተመረጡ መምህራን ማስተማር ከጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ዓመታት (5ዙር) ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ሲያሳልፍ የቆየ ሲሆን በዘንድሮው 100% በማሳለፍ እንደሀገር ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል ።ውጤቱ ቤተሰብን ፣ የትምህርት ቢሮን እና በአጠቃላይ የትምህርቱን ማህበረሰብ ያኮራ ውጤት ነውና ለዚህ ውጤት መምጣት ሌት ተቀን የለፋችሁ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ሠራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም የተማሪዎች ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ።
✔️ ከሁሉ በላይ ውድ የነገ የሀገራችን ተስፋ የሆናችሁ ተማሪዎቻችን ባስመዘገባችሁት ውጤት ኮርተንባችኃል።
እንኳን ደስ አላችሁ።
ብርሃነመስቀል ጠና ( ዶ/ር )
የኮትዩ ፕሬዚዳንት

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለው ጠንካራ ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ዛሬ ነሀሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ተቋሙ እያካሄዳቸው ያላቸውን የመሠረተ ልማት አውታሮች እና ዩኒቨርሲቲውን የማቋቋም ሥራ ያለበትን ጎብኝተዋል፡፡ለማህበረሰብ ተወካዮቹ በተደረገው ማስጎብኘት ገለጻ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ሲሆኑ በገለጻቸውም ተቋሙን ቀደም ስንቀበል ከማንም በላይ የያኔው ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የነበረበትን ደረጃ ታስታውሳላችሁ አሁን ካለበትም ለማነፃፀር ትክክለኛ ዓይን የናንተ ነው፤ ፍፁም ተረስቶ ብቻ ሳይሆን ተትቶ የቆየ ሲሆን አሁን በለውጡ በመልሶ ማደራጀት የሀገሪቱ ብቸኛ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ሲታወጅ ከአባባል ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን መሠረተልማት የሚመጥን ለማድረግ መንግስት ፕሮጀክቶችን ፈቅዶ ለተልዕኮው የሚመጥን እንዲሆን በሙሉ ቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን። በመሆኑም ሥራችንን ለማየትና ከወዲሁ አስተያየታችሁን ልትለግሱን የህብረተሰቡን አስተያየት ይዛችሁ ልትጎበኙን በመምጣታችሁ ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።አያይዘውም በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን ለተሰጠው ተልዕኮ ምቹ፣ በተማሪዎች ተመራጭ እና ተወዳዳሪ የሚያደርጉት የመሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች እየተገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ብርሃነመስቀል፣ ግንባታዎቹ ሲጠናቀቁ ለተልዕኮው መወጣት ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን የምትረዱት ሆኖ በተጓዳኝ ለአካባቢው መልካም ገጽታን ከማላበስና አካባቢውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛነት አብራርተውላቸዋል ።የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ወንድሙ ግዛው በበኩላቸውበሁሉ ክልል መሠረት እየተጣለ አንድ ተብሎ ዩኒቨርሲቲ ሲገነባ ይሄኛው ስንቱን መምህር እያስተማረ ለሀገር ያበረከተ ተቋም ለምን በቀደመው ሥርዓት ተጥሎ እንደቆየ ሁሌ ስናዝን የኖርን ሲሆን በለውጡ እና ይህ አሁን ያለው አመራር ከመጣ የታየው ለውጥ የሚደነቅ ነው ያሉት ተወካዩ እንቅስቃሴያችሁን እና የየተቋሙን የየዕለት ተዕለት ለውጥ ማህበረሰቡ በቅርበት እንደሚከታተልና በዚህም ለዩኒቨርሲቲው አመራር ከፍተኛ ከበረታ እንዳለው አስረድተዋል።አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት ቤቶችን በማገዝና በማዘመን ፣ ለአከባቢው አልፎ ተርፎም ለከተማው ወጣቶች የተለያዩ ሙያዊ ሥልጠናዎችን በመስጠት በተለይም በባህሪይ እነፃ እያደረገ ያለው ሥራ ፣ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ተግባራት ለአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ላለው ድጋፍና እገዛዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በጉብኝታቸው በተመለከቱት ነገር መደነቃቸውንና ዩኒቨርሲቲው እየተጓዘበት ባለው ከፍተኛ ተቋማዊ እድገት መደሰታቸውን ገልጸው፣ ማንኛውንም እገዛ ለማድረግ እንደሁልጊዜው ከተቋሙ ጎን እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል ፡፡
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

The Second Round KUE-CUE ICT and Science Teachers in-Service Joint Training Concluded Successfully

The Second Round KUE-CUE ICT and Science Teachers in-Service Joint Training that was spanned from August 26-30, 2024, for five consecutive day was successfully concluded on Friday August 30, 2024. The training aims at strengthening the capacity of Science and ICT education teachers through targeted in-service training programs.

On the opening event, Dr. Dejen Chaka welcomed the Korean delegation, KUE Instructors and the teacher trainees on behalf of Dr. Berhanemeskel Tena, the President of Kotebe University of Education.  Dr, Dejen remarked on this event that To date, this initiative has successfully reached 18 secondary and 41 elementary schools in total 59 schools within Addis Ababa City Administration. As a result, 148 Science and ICT teachers have benefited from this program which enhances their skills and knowledge to better serve their students, and of course your nation.

Professor Kim Hyun Joo, the General Manager of the 2023 Civil Society Partnership Program/KOICA Project, welcomed instructors and trainee teachers to the second round of teacher training held at KUE from August 26-30, 2024. She expressed gratitude to Dr. Berhanemeskel Tena, President of Kotebe University of Education, for his collaboration and to Dr. Dejen Chaka, the Coordinator, and the project team for their dedication. Professor Kim noted the historical support of Ethiopian soldiers during the Korean War and emphasized the importance of mutual aid, stating that Korea now aims to support Ethiopia. Additionally, she expressed optimism about achieving shared goals and producing successful students through the hard work of the trained teachers.

It was evidenced that the training initiated through the 2023 Civil Society Partnership Program (2023 CSPP/KOICA) supported by KOICA financially.

Kotebe University of Education Concluded Training for Trainers of Trainees

Kotebe University of Education has successfully concluded training for Trainers of Trainees, equipping them to lead a summer capacity building initiative for secondary school teachers and school leaders. The training, which commenced yesterday and concluded today, July 24, 2024, aimed to bolster the skills and knowledge of educators across the nation.

During his closing remarks, Dr. Berhanemeskel Tena, President of Kotebe University of Education, expressed his confidence that the training had provided participants with the necessary tools for success. He emphasized the importance of discipline and accountability throughout the training process, highlighting that this program represents a significant investment by the government, particularly the Ministry of Education.

The upcoming summer capacity building training for secondary school teachers and school leaders, scheduled to begin on July 29, 2024, will be closely monitored by a task force chaired by the University President.

Public and International Relations Office

የ2016 ዓ.ም ልዩ የክረምት መርሐግብር የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመውሰድ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ሰልጣኞች በሙሉ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር ለልዩ የክረምት መርሐግብር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንድትወስዱ በዩኒቨርሲቲው የተመደባችሁ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ አውቃችሁ፣ በዕለቱ በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ዕለት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ሰልጣኝ በምንም ሁኔታ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ

ወደ ዩኒቨርስቲው ስትመጡ ፦

    1. ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
    2. ከኦሮሚያ የምትመጡ ሰልጣኞች የራሳችሁን ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
    3. ከአዲስ አበባ የምትመጡ በተመላላሽነት ስለምትስተናገዱ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ማምጣት አይጠበቅባችሁም።
    4. ከኦሮሚያ የምትመጡ ሰልጣኞች በዕለቱ ከ 2:30-3:30 ከአዲስ አበባ የምትመጡ ደግሞ ከ6:30 -7:30 ሰዓት በዩኒቨርሲቲ ግቢ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ ፤
    5. ከአዲስ አበባ የምትመጡ ለመኝታ እና ለምግብ የተያዘላችሁ በጀት በካሽ የሚሠጣችሁ ይሆናል።

                                                                                                                                                          ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በታሪካዊው የዓድዋ መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ. ም

በመማር ማስተማር ሂደት ስድስት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው አንጋፋው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 868 ወንድ፤ 812 ደግሞ ሴት፤ በድምሩ 1680 ተማሪዎችን በታሪካዊው የዓድዋ መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ ከፍተኛ የመንግሰት አመራሮች፣ ዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና የቦርድ አባላት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የሴኔት አባላት በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና በምረቃ ስነ-ስርዓቱ መክፈቻ ባስተላለፋት መልዕክት ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በመማር ማስተማር ሂደት በርካታ ውጣ ውረዶችን በማለፍና አያሌ ስኬቶችን በማስመዝገብ ለዚህ ደረጃ መድረሱን ጠቆመው መንግሥትም የአገሪቷን የትምህርት ችግር ለመቅረፍ ካለው ፅኑ ፍላጎት በመነሳት መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተወሰነው ውሳኔ መሠረት “ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ መደረጉንና በአሁኑ ወቅትም ብቸኛ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መሆኑንና አመልክተዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ፣ ሀገሪቱ የምትፈልገውን የተማረ የሰው ኃይል በሟሟላት ረገድ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን አስተዋፅዖ ሲያበረክት የቆየ ሲሆን፣ አሁንም መንግሥት በሰጠው ልዩ ተልዕኮ መሠረት የትምህርት ስብራቱን ለመጠገን በአዲስ አወቃቀርና አደረጃጀት ፍኖተ ካርታ ነድፎና አዲስ የካሪኩለም ማዕቀፍ ቀርጾ የተሻሉ የትምህርት ባለሙያዎችን ለማፍራት ከምንጊዜውም በላይ እየተጋ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ፤ የመንግስት የኮሚዩኒኬሸን ሚንስትርና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰበሳቢ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራችን በምታደርገው የብልፅግና ጉዞ ዋነኛ መሣሪያው ትምህርት በመሆኑ መንግሰት የትምህርት ተቋማትን ከማስፋፋት በዘለለ በትምህርት ጥራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ በመቀጠልም ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ “እየገነባን እናስተምራለን፤ እያስተማርን እንገነበለን“ በሚል መሪ ቃል በአዲስ የለውጥ ጎዳና ላይ እንደሚገኝ ተናግረው፣ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ጥራት፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ እየሠራ ያለው ተጨባጭ ውጤታማ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣም ምሩቃንም በሥነምግባር የታነፁ ከአድልኦ የፀዱ ሁሉንም እኩል የሚያገለግሉ የመልካም ስብዕና ተምሳሌት እንዲሆኑ እና ከሙስናና ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር ለ2016 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የተዘጋጀውን የመውጫ ፈተና ለተማሪዎቻቸው ከፍተኛ ሙያዊ እገዛ በማድረግ ተማሪዎቻቸው ፈተናውን ሙሉ በሙሉ እንዲያልፉ ላደረጉ ኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች የእውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሽልማት፣ የምስክር ወረቀትና የእውቅና አሰጣጥ ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ 37 A+ በድምሩ 3.99 ነጥብ በማስመዝገብ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበች ሴት ተማሪ ዩኒቨርሲቲው ልዩ ሽልማት እና የሁለተኛ ዲግሪ ሙሉ ስኮላርሺፕ ያበረከተላት ሲሆን በተመሳሳይ 36 A+ በድምሩ 3.99 ነጥብ በማስመዝገብ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላመጣ አንድ ወንድ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ ዲግሪ ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሕዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት

 

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ወራሪው ጁንታ ላፈናቀላቸው ወገኖቻችን ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ ሰጠ፡፡

                                                                                                                                                                    25/03/2014 ዓ.ም

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ለወገን አሌኝታነቱን በተግባር ለመግልፅ ያደረገው ድጋፍ በወራሪው ጁንታ ምክንያት ተፈናቅለው በደብረብርሃን ከተማ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖቻችን እንደሆነ ተውቋል፡፡ ድጋፉ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሰባሰቡ ምግብ ነክ፣ አልባሳት፤ የተለያዩ ቁሳቁሶችና የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን ያካተተ ሲሆን በገንዘብ ሲሰላ 1.2 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚሁ ወቅት ወራሪ የህዝብ ጠላት በሆነው ጁንታ ታጣቂ የተፈናቀሉት ወገኖችና በጦርነቱ የተጎዱ ጄግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባለት የተጎበኙ ሲሆን ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ያሉትና በጦርነቱ ተጎድተው በማገገም ላይ የሚገኙ ወገኖች በተደረገው የደጀንነት ተግባር መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለወገን አሌኝታነታቸውን ለማግለፅ በእለቱ በከተማው የተገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን በመወከል ባደረጉት ንግግራቸው የአጥፊዎች ሴራና የአውዳሚዎች ተግባር በመላው የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያዊያን ደጀንነት መደገፍና መመከት ስላለበት ይህንኑ ተግባራቸውን ለመወጣት ዩኒቨርሲቲዎቸ እውቀትን አፍልቆ ከማስተማር ባሻገር ያላቸውን ጥሪት በማካፈል ያደረጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፆ ለወደፊትም ችግሩ በዘለቄታዊነት እስከሚቀረፍ ድረስ ድጋፉ ቀጠይነት እንዳለው ተናግሯል፡፡ እንዲሁም በስፍራው ካለው የመከላከያ ሠራዊታችን ጋር በነበረው መርሀ-ግብር ላይ እንደተናገሩት ጄግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጠላትን እየመከቱ፤ ድባቅ እየመቱ፤ በአጥንታቸው ሀገርን እየገነቡ፤ ኒዮ-ኮሎኒያሊዝምን እያሸነፉ በደማቸው ደግሞ አኩሪ የድል ታሪክን እየፃፉ ስለሆኑ እጅግ ኮርተንባቸዋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከአሁን ቀደም በወራሪው ጁንታ ጦርነት ምክንያት ከአፋር ክልል እና ከወሎ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ዩኒቨርሲቲው የአምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

                                                                                                                      የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ የሽግግር ሂዳትን አስመልክቶ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

                                                                                                                                                                            17/03/2014 ዓ.ም
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት በዋና ግቢው የተቋሙን ሽግግር ሂዳት አስመልክቶ ጥልቅ ውይይት አካሄዷል፡፡ በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና የተቋሙ ታሪካዊ ዳራና ችግሮቹ እንዲሁም የወደፊት ትኩረት አቅጣጫዎቹ ላይ በማተኮር ለውይይት መነሻ የሚሆን ገላጭ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የትምህርት ልህቀት፣ የምርምር ስርፀት፣ የዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ፣ መልካም አስተዳደራዊና የስራ አመራር ለውጥ፣ ማህበረሰባዊ ተሳትፎን ማሳደግ፣ ገበያ-መር በሆነ መልክ የተቋሙን ፕሮግራሞች በመቃኘትና በአዋጅ 1263/2014 የተሰጠውን የትምህርት ዩኒቨርሲቲነትን ተልዕኮ በብቃት መወጣት የተቋሙ የወደፊት የትኩራት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለሀገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት ምክንያቶቹና ለችግሮቹ መፍትሄ ናቸው ብለው ያሉዋቸውን ቁምነገሮች ከዘረዘሩ በኋላ የስራ መመሪያና የዩኒቨርሲቲውን የወደፊት ትኩረት አቅጣጫ ሲያመላክቱ እንደተናገሩት እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በኃላፊነትና በተቆርቋሪነት ለዩኒቨርሲቲው አዲስ በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ ምክክር ላይ በንቃት በመሳተፍ በአገራችን የትምህርት ጥራት ለውጥ እንዲመጣ በትጋት በመስራት ልዩ አስተዋፅኦ ማበርከት ከዩኒቨርሲቲው እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መንግስት ከዩኒቨርሲቲው የሚጠብቀው ለውጥ፣ ጥገናዊ ሳይሆን መሠረታዊ ለውጥ እንደሆነ አስምሮበት ለዚሁ ተልዕኮ ዩኒቨርሲቲው ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት አሳስቧል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት