ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ የሽግግር ሂዳትን አስመልክቶ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

                                                                                                                                                                            17/03/2014 ዓ.ም
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት በዋና ግቢው የተቋሙን ሽግግር ሂዳት አስመልክቶ ጥልቅ ውይይት አካሄዷል፡፡ በዚሁ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና የተቋሙ ታሪካዊ ዳራና ችግሮቹ እንዲሁም የወደፊት ትኩረት አቅጣጫዎቹ ላይ በማተኮር ለውይይት መነሻ የሚሆን ገላጭ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የትምህርት ልህቀት፣ የምርምር ስርፀት፣ የዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ፣ መልካም አስተዳደራዊና የስራ አመራር ለውጥ፣ ማህበረሰባዊ ተሳትፎን ማሳደግ፣ ገበያ-መር በሆነ መልክ የተቋሙን ፕሮግራሞች በመቃኘትና በአዋጅ 1263/2014 የተሰጠውን የትምህርት ዩኒቨርሲቲነትን ተልዕኮ በብቃት መወጣት የተቋሙ የወደፊት የትኩራት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለሀገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት ምክንያቶቹና ለችግሮቹ መፍትሄ ናቸው ብለው ያሉዋቸውን ቁምነገሮች ከዘረዘሩ በኋላ የስራ መመሪያና የዩኒቨርሲቲውን የወደፊት ትኩረት አቅጣጫ ሲያመላክቱ እንደተናገሩት እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በኃላፊነትና በተቆርቋሪነት ለዩኒቨርሲቲው አዲስ በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ ምክክር ላይ በንቃት በመሳተፍ በአገራችን የትምህርት ጥራት ለውጥ እንዲመጣ በትጋት በመስራት ልዩ አስተዋፅኦ ማበርከት ከዩኒቨርሲቲው እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መንግስት ከዩኒቨርሲቲው የሚጠብቀው ለውጥ፣ ጥገናዊ ሳይሆን መሠረታዊ ለውጥ እንደሆነ አስምሮበት ለዚሁ ተልዕኮ ዩኒቨርሲቲው ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት አሳስቧል፡፡
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
 

Kotebe Metropolitan University

Kotebe University of Education (KUE) Undertakes Budgetary Training Deemed Necessary for Institutional Transformation

******************************************

As KUE prepares itself to undertake institutional transformational from Metropolitan development oriented programm to University of Education , which could be the first of its kind in the history of the Nation in a century, is giving training to its leaders on how to prepare and use the Federal programm budget. On his opening speech, Honorable Dr. Berhanemeskel Tena, the President, underling the significance of the training to the effective transition being underway, encouraged the trainees to actively participate in the training.

Experienced professionals from the Ministry of Finance are delivering the training.

                                                                                                         

                                                                                                      Communications Affairs Directorate

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሚሰራቸው ጥናቶችና ምርምሮች ውጤታማና ችግር ፈቺ መሆናቸው ተገለፀ፡፡

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ መከላከል ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአዲስ አበባ ከተማንና የአካባቢዋን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ ባለመው የጥናት ኘሮጀክት ዙሪያ ግብዓት ለማሰባሰብ በቶኘ ቴን ሆቴል በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የቀድሞው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የአሁኑ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሚሰራቸው ጥናቶችና ምርምሮች ማህበረሰብ ተኮር፣ ውጤታማና ችግር ፈቺ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡  

ዩኒቨርሲቲው በእስካሁኑ ሂደት ከከተማው አስተዳደር ቢሮዎች ጋር በመተባበር የሰራቸው ጥናቶች በቅርቡ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት በማስመልከት የተሰራውን ጥናት ጨምሮ ሁሉም ጥናቶች ውጤታማ እንደነበሩ የጠቀሱት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና፣ ዩኒቨርሲቲው ጥናቶችንና ምርምሮችን ሲሰራ ለገንዘብ ብሎ ሳይሆን በተግባር የማህበረሰብን ችግር ለመፍታት አልሞ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡በተመሳሳይ መልኩ አሁን እየተሰራ ያለው ስራ የከተማዋን ችግር ሊፈታ የሚችል እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ የገለፁት ኘሬዝዳንቱ ይህ ጥናት የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ወደ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከተቀየረ ወዲህ የመጀመሪያው እንደሚሆንና ለጥናቱም የእስካሁኑ ሂደት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ መከላከል ኮሚሽን ድርሻ ጉልህ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአውደ ጥናቱን ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህብረሰብ ምክትል ኘሬዝዳንት ዶክተር ጠና በቀለ፣ ጥናቱ በሃገራችን ታሪክ የመጀመሪያውና ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራ እንደመሆኑ ለሌሎች ከተሞችም አርአያ ስለሚሆን ለኘሮጀክቱ ስኬታማነት ግብዓት የሚሆን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሙያዊ አስተያየት እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል፡፡ በዚሁ የምክክር መድረክ የጥናቱን ሂደት የሚያመለክቱ መነሻ ትልመ ጥናቶች በዶ/ር በሊና ተርፋሳ፣ በዶክተር ብርሃኑ እንደሻውና በዶክተር ቱሉ ቶላ የቀረበ ሲሆን በጥናት ቡድኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እተየሰራ ያለው ስራ ገና ከጅመሩ ብዙ የታለፈበትና በቀጣይም ሲጠናቀቅ የከተማዋን ብሎም ዙሪያዋ የሚገኙ አካባቢዎችን ችግር ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑንም የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች አስተያየት የተሰጠበት የተሳከ የውይይት መድረክ መሆኑን ለማወቅ ተችላል፡፡  

 

                                                                                                                    የኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት                                                            

ለአንደኛ ዓመት (አዲስ የተመዘገባችሁ) የማታና እረፍት ቀናት ዲግሪና ዲፕሎማ ተማሪዎች በሙሉ

1ኛ. ካመለከታችሁበት የትምህርት ክፍል Username እና Password ወስዳችሁ ፕሮፋይል አዘጋችታችሁ ነገር ግን ክፍያ በCBE Birr ያልከፈላችሁ ተማሪዎች ብቻ ማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን እና ረቡዕ ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በኦንላይን ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እና ክፍያ በCBE Birr እንድትፈጽሙ እንዲሁ

2ኛ. ትምህርት የተጀመረ በመሆኑ የኮሌጅ/ፋኩልቲ/አካዳሚ የተከታታይና ርቀት ትምህርት አስተባባሪዎች ባወጡት የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ትምህርታችሁን መከታተል እንድትጀመሩ እናሳስባለን፡፡

 

                                                                                                                                  የኮሜዩ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት

ለመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ

             ሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲያችን በአዲስ ዘመን ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን እና የዓመቱን የተማሪዎች ምርቃት በማስመልከት ኘሮግራም  ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ህንፃ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ እንድትገኙ እያሳሰብን በተለመደው መልኩ በሁሉም መስመሮች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

                                                                                                                                                                                              ዩኒቨርሲቲው

ማስታወቂያ ለአዲስ እና ነባር ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች

በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ድረገጽ ለመመዝገብ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመ በአጭር ጊዜ ውስጥ እስክናስተካክል እንድትታገሱን ከይቅርታ ጋር እየጠየቅን የምዝገባ ጊዜውን ለተወሰነ ጊዜ እንደምናራዝም እናሳስባለን።
ድህረ-ምረቃ እና ሬጂስትራር   ጥቅምት 04/2014 ዓም