ኮትዩ ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የህይወት ክሂሎት ሥልጠና ሰጠ።

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ግንቦት 12/ 2014ዓ.ም የህይወት ክሂሎት ሥልጠና ያዘጋጀ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ጊዜያዊ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሽመልስ ዘውዴ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ከቤተሰባቸው ርቀው ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ዋና ዓላማቸው ትምህርት በመሆኑ፣ ይህንኑ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ በጥንቃቄ መጓዝ አለባቸው ብለዋል።
የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ዓላማቸውን ከሚያሰናክሉ ተግባራት መቆጠብ፣ በአልባሌ ሥፍራዎች እና ተግባራት ላይ አለመሳተፍ፣ የስነተዋልዶ ጤና ችግር የሚያስከትልባቸውን ጉዳት ቀድመው በማወቅ ጥንቃቄ ማድረግ፣ በትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ውጤታማ ሆነው ለምርቃት እንዲበቁ እና ይህንንም ለማሳካት ሥልጠናው ጠቃሚ በመሆኑ፣ በትኩረት እንዲከታተሉ ዶ/ር ሽመልስ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አባይ በላይሁን የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመጡበት ወቅት በተደረገላቸው አቀባበል አማካኝነት የቤተሰባዊነት ስሜት እና ጥሩ መቀራረብ መፈጠሩን አስታውሰው፣ አሁን የተዘጋጀው ሥልጠናም ተማሪዎቻችን በዩኒቨርሲቲው በሚቆዩባቸው ጊዜያት ማወቅ የሚገባቸውን ልዩ ልዩ የህይወት ክሂሎቶች በማስገንዘብ በኩል እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ፣ ሥልጠናውን በንቃት መከታተል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምኞት ጌታቸው የስራ ክፍላቸው የስነተዋልዶ እና ተያያዥ ጉዳዮች ስልጠና እንዲሁም ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስን በተመለከተ ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኙ ወገኖች አስፈላጊውን መረጃ እና አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በሥልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎቱን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ የሥልጠናውን መርሐ ግብር መሠረት በማድረግ በግል እድገት (Personal Development)፣ በማህበራዊ ክሂሎት፣ በትምህርት ክሂሎት፣ በስነተዋልዶ ጤና እና ጎጂ ባህርያት ዙሪያ ለተማሪዎች ገለፃ ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል።
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
May be an image of one or more people, people sitting and indoor
May be an image of 1 person, standing and indoor
May be an image of 5 people, people sitting and indoor
May be an image of 5 people, people sitting and indoor
May be an image of 1 person, sitting, standing and indoor
Posted in Office of the Communication Affairs.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *