Skip to content

ለዩኒቨርሲቲው የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው

(ኮትዩ፣ ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም) – ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች የተዘጋጀውና ከህዳር 3-10/2018 ዓ.ም በሁለት ዙር የሚሰጠው የሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በተጀመረበት ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያሰሙት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች ዋና ተግባር የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እና ንብረት ደህንነት በመጠበቅ የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮዎች እንዲሳኩ ማድረግ መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንኑ ኃላፊነትም በአግባቡ ለመወጣትና የሰላምና ደህንነት አገልግሎቱም እያደገ እና እየረቀቀ እንዲሄድ የዚህ ዓይነቱ የአቅም ግንባታ ስልጠና ወሳኝ በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እና በነቃ ተሳትፎ እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የተዘጋጀው ከዚህ በፊት በሥራው ሂደት ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህ ረገድ ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው የየሺፍቱ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች በሙሉ ያለምንም መጓደል ስልጠናወን መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደጊያ ኃላፊ ኢንስፔክተር አለማየሁ አርጋው ሲሆኑ፣ ስልጠናውም የጥበቃ ምንነት፣ የጥበቃ ዓይነቶችንና ዘዴዎች፣ በሥራ ላይ ስለሚኖር ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ በጥበቃ ቦታ ላይ የሚያጋጥሙ የችግር አፈታት ዘዴዎችን እና ተያያዥ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ተግባራት በመሳሰሉት ይዘቶች የተዘጋጀ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *