Skip to content

ለዩኒቨርሲቲው የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

(ኮትዩ፣ ህዳር 2018 ዓ.ም) – ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች ላለፉት ስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የሥራ ላይ ስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ ባሰሙት ንግግር፣ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት ሠራተኞች የዩኒቨርሲቲውን ተግባራት ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸው፣ ሰልጣኞቹ ለስድስት ቀናት የወሰዱትን የንድፈሃሳብና የተግባር ስልጠና በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ዓለምአቀፍ ተማሪዎችን የሚቀበል በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ተመሳሳይ ስልጠናዎችን ለሠራተኞቹ በማመቻቸት ዘመናዊ የጥበቃ ሥርዓት ተግባራዊ እንዲሆን የተሻሉ ስራዎችን መስራት እንደሚያስፈልግም ፕሬዘዳንቱ ዶ/ር ተሾመ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሰላምና ደህንነት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር አብዲሳ ባይሳ እና ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ኮማንደር በየነ ዴሬሳ፣ ከጥበቃ ምንነት እስከ መሣሪያ አጠቃቀም ድረስ በተግባር የተደገፈው ስልጠና አዲስ እውቀትና ጥሩ ግብዓቶች የተገኙበት መሆኑን ጠቅሰው፣ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ሰልጣኞችም ኃላፊነታቸውን ከቀድሞው በተሻለ አግባብ እንዲወጡ አስገንዝበዋል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ስልጠናው ከስራቸውም በተጨማሪ ለህይወታቸውም ጭምር ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲው ስልጠናውን በማመቻቸቱ አመስግነዋል።
የዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥ ጽ/ቤት ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተስፋዬ ባዬ ባሰሙት የመዝጊያ ንግግር፣ በታታሪነትና በዲሲፕሊን የታገዘው ይህ ስልጠና ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸው፣ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ፣ ስልጠናውን የሰጡ እና ያመቻቹ አካላትን አመስግነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *