ከስፖርት ትጥቅ ባሻገር ያሉ ሀሳቦችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ የስፖርት ትጥቅ ብራንድ ጎፈሬ ለሀገራችን ትልቅ ፋይዳ ያለው ስትራቴጂካዊ ስምምነት በዛሬው ዕለት ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ጋር ተፈራርሟል።
ይህ ለሦስት ዓመታት በሚቆየው ስምምነት ጎፈሬ እና ዩኒቨርስቲው በስፖርት ሳይንስ፣ አካል ብቃት እና ማሕበረሰብ ግንባታ ዙሪያ ጥናቶችን ማጥናት፣ በስፖርት ኢንዱስትሪ ካሪኩለም ዲቭሎፕመንት ላይ የጋራ ስራዎችን መስራት፣ በኢንተርንሺፕ እና ትሬኒንግ ዙሪያ አብሮ መስራት፣ ለስፖርቱ የሚጠቅሙ ወርክ ሾፕ፣ ሴሚናር፣ ኢቨንት እና ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀት፣ ስፖርት ለማኅበረሰብ እድገት ስላለው ፋይዳ ስራዎን መስራት እንዲሁም በስፖርቱ ያለውን እውቀት ለማሳደግ እና የእውቀት ልውውጥ እንዲኖር መስራት በሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ስምምነት መፈፀማቸው ታውቋል።
በስምምነቱ ወቅት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ባደረጉት ንግግርጎፈሬ በስፖርት ኢንዱስትሪው ውስጥ የደረሰበትን ደረጃ አድንቀው ስፖርቱን ለማሳደግ በቀጣዮቹ ዓመታት ለተሻለ ውጤት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
አቶ ሳሙኤል በበኩላቸው ስትራቴጂካሊ የኢትዮጵያን ስፖርት የሚያሳድጉ ሀሳቦችን በማፍለቅ የሚታወቀው ተቋማቸው አሁን ደግሞ የዕውቀት ማዕከል ከሆነው ዩኒቨርስቲ ጋር ለመስራት ስምምነት በማድረጋቸው ደስተኛ እንደሆኑ አመልክተዋል።