በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ እና አጎራባች ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የግል እና የመንግስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪ እና የባዮሎጂ መምህራን ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ዶ/ር ቅድስት ዮሐንስ ፤ የምር/ማ/አገ/ጊ/ም/ፕ እንዳሉት እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች ለተሻለ የመማር ማስተማር ሥራ ያላቸው አስተዋጽኦ ከሚባለው በላይ ነው።