(ኮትዩ ፣ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም) – የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎች ጋር በዩኒቨርሲቲው የአሠራርና የለውጥ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የሁለት አዲስ ምክትል ፕሬዘዳንቶችን ሹመትንም አሳውቀዋል።
አዲሶቹ ምክትል ፕሬዘዳንቶች፣ የዩኒቨርሲቲውን አካዳሚክ ጉዳዮች ጽ/ቤት በምክትል ፕሬዘዳንትነት ሲመሩ በነበሩት ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ ምትክ ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ፤ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ጽ/ቤት ሲመሩት በነበሩት ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ ምትክ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ የተመደቡ መሆናቸው ታውቋል።
ለሁለቱ የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንቶች የምስጋና እና ሽኝት፣ እንዲሁም በምትኩ ለተመደቡት አዲስ ምክትል ፕሬዘዳንቶች ደግሞ የትውውቅ መርሐግብርም ተደርጓል።




