Skip to content

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተቋማዊ ዳግም ምዝገባ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ ተቋሙ የሚጠበቅበትን ሰነዶችና ግብአቶች አሟልቶ ዳግም ምዝገባውን ያካሂድ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሸምሱ ጂሀድ የምዝገባውን ዓላማ፣ የሚያስፈልጉ ግበአቶች እና ስለሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች አስገንዝበው ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ከተሰጠ በኃላ ምዝገባውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅች ተሟልተው ዳግም ምዝገባው እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የዳግም ምዝገባው አፈጻጸም ዝግጅት የተጀመረው የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *