(ጅማ፣ ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም) — በጅማ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘውና 4ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ውድድር፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በሌጣ ፈረስ የግል የበላይነትና በመሳሪያ ጅምናስቲክስ 2 የብር ሜዳሊያዎችን ያሸነፈ ሲሆን፣ በተጨማሪም በትይዩ ጥንድ አግዳሚ ዘንግ፣ በወለል ጅምናስቲክስና በሁሉም አጠቃላይ ጅምናስቲክስ ውድድሮች 3 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በድምሩ 5 ሜዳሊያዎችን በማግኘት የጅምናስቲክስ ውድድሩን በስኬት አጠናቋል።
የሜዳሊያ ሽልማቱንም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማኅበር ፕሬዘዳንት አቶ አባይ በላይሁን እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለተማሪ ስፖርተኞቹ አበርክተዋል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በወንዶች ቴኒስ እና በሴቶች የሦስት በሦስት (3×3) የቅርጫት ኳስ ውድድር ተጋጣሚዎቹን በሰፊ ልዩነት በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።







