ኮትዩ፣ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በቅድመ አንደኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ትምህርቶች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከሚሠራው RIGHT TO PLAY ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ስምነት ተፈራርሟል።
በፊርማ ሥነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ RIGHT TO PLAY IN ETHIOPIA ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመሥራት በመወሰኑ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት ጠቃሚና ውጤታማ ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የዛሬው ስምምነታቸው መሠረት እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የRIGHT TO PLAY IN ETHIOPIA ዳይሬክተር አቶ ተድላ ታከለ በበኩላቸው RIGHT TO PLAY በቅድመ አንደኛ እና በመጀመርያ ደረጃ ትምህርቶች ዙሪያ ከ20 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር play-based curriculum (በጨዋታ ማስተማር) ላይ ሲሰራ በመቆየቱ፣ በዘርፉ ያካበተውን ልምድ ብቸኛ ከሆነው የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መሥራቱ ትልቅ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር ስለሚያደርግ ለሀገር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።