(ጅማ፣ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም) – በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ውድድር፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በወንዶች የቦርድ ቼዝ ጨዋታ 1 የወርቅ፣ እንዲሁም በሴቶች የቼዝ ጨዋታ 1 ወርቅ እና 1 የነሐስ በድምሩ 2 የወርቅ እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች አሸናፊ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች እና ሴቶች ጥንድ የቴኒስ ጨዋታ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኢንጂባራ ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 2 በማሸነፍ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ውስጥ ገብቷል፡፡



