Skip to content

“ዛሬ የምንተክለው ለልጆቻችን ነው!” … ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና

green Legacy
“በመትከል ማንሰራራት!” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለማስቀጠል የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
በወንድይራድ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በዩኒቨርሲቲው ቅፅር ግቢ የተካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሐግብር ያስጀመሩት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ የዘንድሮው ችግኝ ተከላ በዩኒቨርሲቲያችን ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን አስታውሰው፣ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዙሮች በጫካ ፕሮጀክት፣ ሦስተኛው በወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መካሄዱንና ችግኞቹም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም፣ የዘንድሮው በዩኒቨርሲቲው ቅፅር ግቢ ውስጥ ካካሄድነው መትከል በተጨማሪ
በወንድይራድ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተክለናል። ትምህርት ቤትን የመረጥነውም ዩኒቨርሲቲው ትውልድን የሚቀርፅ በመሆኑ ተማሪዎች ከአርአያነታችን ፣ መትከልንም እንዲያዩ እና እንዲለማመዱ ፣ችግኞቹንም
እንዲንከባከቡ በማሰብ ነው ። ዛሬ የምንተክለው ነገን ነው፤ የተከልነውም ለልጆቻችን ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ፣ ችግኞቹ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ለምግብነት በመዋል የተማሪዎችን የምገባ ሥርዓት የሚደግፉ ብሎም ለትምህርት ቤቱ የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተከላቸውን ችግኞች መንከባከብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባካሄደው የችግኝ ተከላ፣ አንድ ሺህ የአቮካዶ እና የአፕል ችግኞች መተከላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *