“የቋንቋ መምህራን ተማሪዎች ቋንቋውን በፍላጎት እና በፍቅር እንዲማሩ እና እንዲለምዱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትብብር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ቋንቋዎችን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራን የሥራ ላይ ሥልጠና ተሠጠ፡፡
በስልጠናው መክፈቻ የቋንቋ መምህራን ተማሪዎቻቸው ያሉበትን ደረጃ ጠንቅቀው በመረዳት ከመሠረታዊው የቋንቋ ክሂሎት በተጓዳኝ ቋንቋውን በፍላጎት እና በፍቅር እንዲማሩ፣ እንዲለምዱ እና እንዲናገሩ ማስቻል ለዚህም የቋንቋ መምህራን የሁለተኛ ቋንቋን የማስተማርያ ስነዘዴዎችን (Method of Teaching) ጠንቅቀው ማወቅ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፣ በተጨማሪም መምህራን በሙያቸውም ተወዳዳሪ ሆነው ለመገኘትም የትምህርት እርከናቸውን በየጊዜው ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸውና ለዚህም ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሁልጊዜም አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ሁሉ እየሰጠ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *