(ኮትዩ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም)- የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ በካሄደው ምርጫ፣ ተማሪ ኃይለአምላክ አያሌው የህብረቱ ፕሬዘዳንት፣ ተማሪ ኤልያስ ያዴታ ምክትል ፕሬዘዳንት፣ ተማሪ ሜሮን አዲሱ ጸሐፊ እንዲሁም ተማሪ መዳዊ አብዱ የሴቶች ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
የምርጫውን ሂደት በንግግር የከፈቱት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ የተማሪዎች ህብረት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ተማሪዎች፣ የዲሞክራሲ ስርዓትን ሂደቶች የሚለማዱበት ከመሆኑም ባሻጋር ብዙ ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን የሚያስፈጽሙበት አደረጃጀት እንደሆነ አስታውሰው፣ የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የወከሏቸውን ተማሪዎች በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ለዚህም የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከጎናቸው በመሆን እንደሚደግፋቸው ጨምረው ገልጸዋል።





