“የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ!” በተሰኘው ሀገራዊ መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችየምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ!” በተሰኘው ሀገራዊ መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

የችግኝ ተከላው በወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከላውን ያስጀመሩት ፕሬዘዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ሀገርና ትውልድን ለማስቀጠል “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ!” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል እየተደረገ ያለውን የችግኝ ተከላ ማስቀጠል ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ( ዶ/ር) የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብርን እውን ለማድረግ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዙሮች በተለያዩ ቦታዎች የችግኝ ተከላ ማካሄዱን ያስታወሱት ፕሬዘዳንቱ፣ የዘንድሮው ችግኝ ተከላ መርሐግብርም ለዩኒቨርሲቲው ቅርብ በሆነው በወንድይራድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከናወኑ ችግኞቹን በቅርበት ለመንከባከብ ምቹ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ችግኞቹን ተመላልሶ እንዲንከባከብ አደራ ብለዋል፡፡

 

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳ 11 ጽ/ቤት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ወርቁ በበኩላቸው፣ በዚህ ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ በመገኘት ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር አሻራቸውን ለማሳረፍ በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በወንድይራድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በወረዳ 11 ጽ/ቤት በጋራ በተካሄደው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሐግብር የማንጎ፣ የአቮካዶ እና የዘይቱን ችግኞች መተከላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *