የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን የዩኒቨርሲቲውን ሁለገብ የተማሪዎች ክሊኒክ፣ የተማሪዎች መመገቢያና የመምህራን ላውንጅ ፣ የአንድ ማዕከል የተማሪዎችአግልግሎት ህንፃዎች እንዲሁም አጠቃላይ የተቋሙን የአጥር ግንባታዎች ያሉበትን ገምግሟል፡፡
በአካላዊ ምልከታው ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፣ ፕሮጀክቶቹ ቦርዱ በየጊዜው በመገምገም በሚሰጠው አቅጣጫና ገንቢ አስተያየቶች መሠረት በከፍተኛ ትጋትና የጥራት ደረጃ እየተገነቡ መሆናቸውን ገልጸው፣ እነዚህ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አሁን የመጨረሻ የግንባታ ደረጃ ላይ እንደሚገኙና በቅርብ ተጠናቅቀው ለምረቃ ዝግጁ እንደሚሆኑ ገልፀዋል ፡፡ ለዚህም የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት ያለመታከት ቀንና ምሽት ጭምር ፕሮጀክቱን እየተከታተለ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ማስቻሉን አስረድተዋል።
የቦርዱ አባላትም ፕሮጀክቶቹ በተሳካ አፈጻጸም ወደመጨረሻው ፍጻሜ መቃረባቸው የዩኒቨርሲቲውን ማኔጅመንት ትጋትና ጥብቅ ክትትል የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይ ሊተኮርባቸው ይገባሉ ባሏቸው ተግባራት ላይ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡