Skip to content

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የ1,500 በላይ ተማሪዎቹን ምረቃ አጸደቀ

(ኮትዩ፣ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም) – የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሴኔት (መማክርት) ዛሬ ባደረገው 3ኛው መደበኛ ስብሰባ በክረምት እና በቅዳሜና እሑድ መርሐግብሮች በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን የ1,573 ተማሪዎች ምረቃ አጽድቋል።
ዶ/ር ወርቃአፈራሁ ስዩም የዩኒቨርርቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ለሴኔቱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ሴኔቱም በመወያየት የ840 ወንድና የ733 ሴት ተማሪዎችን ምረቃ አጽድቋል። ከእነዚህም ተመራቂዎች መካከል 155ቱ በድህረ ምረቃ፣ 20ው በዲፕሎማ፣ 1398ቱ ደግሞ በፒጂዲቲ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *