ከ12 ዩኒቨርሲቲዎች ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች በጋምቤላ ክልል ተገኝተን “በመትከል ማንሳራራት” የሚለውን መሪ ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የችግኝ ተከላ እና በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት እያንዳንዳችን በመውሰድ ግንባታውን በዛሬው ቀን አስጀምረናል።
የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና መገንባት ሲተገብር የቆየው በአመዛኙ አዲስ አበባ ላይ አተኩሮ የነበረው ተሞክሮውን ለማስፋትም ሆነ ለጋራ ሀገረመንግስት ግንባታው የፌዴራል ተቋማት ወደክልሎችም ወጣ ብለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡከክቡር ጠቅላይ ምንስትራችን የተቀመጠው አቅጣጫ አርአያነት ያለው የበጎ ተግባር ሆኖ መተጋገዝን፣ መደጋገፍን፣ መረዳዳትንና መከባበር የበለጠ ለማላቅ እድል የሚሰጥ ነው። በዚሁ አግባብ በምድባችን ገምቤላ ተገኝተን ምግብነት ያላቸው ችግኞችን የተከልን ሲሆን የአቅመደካማ ቤቶችንም ዩኒቨርሲቲው ሊገነባ ሥራውን አስጀምረናል። በአጭር ጊዜ ተሠርቶ እንደሚጠናቀቅም አደራ ከሚወስድልን ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ መግባባት ተደርሷል።