የኮትዩ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የአቪዬሽን ክበብ አባላት ተማሪዎች በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የአቪዬሽን ክበብ አባላት ተማሪዎች በ11/06/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ትምህርታዊ ጉብኝት የአውሮፕላን አብራሪነትን ትምህርትና ስልጠና፣ ስለአየር ትራፊክ እና የአየር ቁጥጥር ማዕከል እንዲሁም የአውሮፕላን ጥገና ክፍሎችን እና አሠራራቸውን በሰፊው ጎብኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የቅድመምረቃ እና ምርምር ዲን ዶ/ር ፍቅሬ ወንድሙ፣ ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሚያሰለጥን በአፍሪካ ብቸኛው የአቭዬሸን ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቁመው፤ ስለአውሮፕላን ዓይነቶች፣ ስለአውሮፕላን ክፍሎች፣ ስለአውሮፕላን አነሳስና አስተራረፍ፣ ስለመንገደኞች ቅድመጥንቃቄዎች፣ ስለአስተናጋጆች እና መስተንግዶ፣ ስለአቪዬሽን ማኔጅመንት እና ኤሮቲካል ኢንጂነሪንግ ንድፈ ሃሳባዊ እና ተግባራዊ ክንውኖች ዝርዝር ገልፀውላቸዋል፡፡
ትምህርታዊ ጉብኝቱ ተማሪዎቹ ስለአቪዬሽን ሳይንስ በሠፊው መረዳት እንደቻሉ ፤ በአጠቃላይም ስለአቪየሸን በማንበብ ያገኙትን ቲዎሪ በተግባር እያንዳንዱን ማየታቸው ያስደሰታቸው መሆኑን ጎብኚ ተማሪዎቹ ገልጸው ዩኒቨርሲቲው ጉብኝቱን ስላመቻቸላቸው አመስግነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *