Skip to content

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች (KPIs) ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ተፈራረመ

(ኮትዩ፣ መስከረም 30/2018 ዓ.ም) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ የታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች (KPIs) ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በካፒታል ሆቴል በተደረገው የፊርማ ሥነስርዓት ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈራረሙት ውል ተግባራዊነት በቁርጠኝነት መስራትና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በየአካባቢያቸው በሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ የትኩረት መስካቸውን ለይተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበው፤ ስምምነቱ በዋናነት መረጃን መሰረት ያደረገ እና ተቆጥሮ የሚመዘን በመሆኑ፣ ዩኒቨርሲቲዎች የወሰዱትን ተግባራት አፈጻጸም ጥራትና ተአማኒነት ባለው መረጃ አስደግፈው ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲም በ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ የታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፣ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሞገስ ባልቻ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ የአፈጻጸም ውል ስምምነቱን ፈርመዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *