Skip to content

አዲሱ የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ከተቋሙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አደረጉ

(ኮትዩ፣ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም) – አዲሱ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅ አደረጉ፡፡
በመርሐግብሩ ላይ ለአዲሱ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ስለዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ገለጻ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት የተደረገላቸው ሲሆን፣ ትኩረት በተሰጣቸው የለውጥ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በመቀጠልም የቦርድ ሰብሳቢው፣ በተቋሙ በመካሄድ ላይ ያሉ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን፣ ልዩ ልዩ የተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን የመሳሰሉትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *