በስልጠናው ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፈቀደ ቱሊ ተቋሙ የሚጠበቅበትን ሰነዶችና ግብአቶች አሟልቶ ዳግም ምዝገባውን ያካሂድ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሸምሱ ጂሀድ የምዝገባውን ዓላማ፣ የሚያስፈልጉ ግበአቶች እና ስለሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች አስገንዝበው ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ከተሰጠ በኃላ ምዝገባውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅች ተሟልተው ዳግም ምዝገባው እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ተደርሷል።




