Skip to content

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል ባንክ አገልግሎት ላይ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ

(ኮትዩ፣ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም) – ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካ ዲስትሪክት ሲቢኢ በጄ የተባለ መተግበሪያን በመጠቀም ለዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ገንዘብ ለመበደርና ለመቆጠብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመወዋል።
የፊርማ ሥነስርዓቱን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ፤ ባንኩ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጋራ ለመስራት ያሳየውን ተነሳሽነት አድንቀዋል። ዶ/ር ተሾመ፣ የዩኒቨርስቲው የገንዘብ እንቅስቃሴዎች በንግድ ባንክ አካውንት በኩል ሲደረጉ መቆየታቸውን በመጥቀስ ከባንኩ ጋር የቆየ ትብብር መኖሩን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ንግድባንክ ማዕከላዊ ሪጅን ም/ፕሬዘዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፣ ሲቢኢ በጄ ሠራተኞች ገንዘባቸውን ባንክ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በእጃቸው በያዙት ሞባይል እንዲቆጥቡ ከማስቻሉም ባሻገር፤ ያለማስያዣ ከ500 ብር እስከ 150 ሺህ ብር ድረስ መበድር ያስችላል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *